በተባበሩት ዓረብ ኢምሬት በሻርጃህ ከተማ 36 ኢትዮጵያውያን ሴቶች ታሰሩ

መስከረም ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢምሬት ኒውስ እንደዘገበው ኢትዮጵያውያኑ በሻርጃህ ፖሊስ የታሠሩት ከስፖንሰሮቻቸው ጠፍተው በመገኘታቸው ነው።

ኢትዮጵያውያኑ  በኢምሬት -አረብ ቪላ ውስጥ እንደሚገኙ መረጃ ከደረሰው በሁዋላ በቁጥጥር ሥር  እንዳዋላቸው የገለጸው የሻርጃህ ፖሊስ፤ በህገ-ወጥ መንገድ በሥራ ተሰማርተው እንደነበር አመልክቷል።

ጉዳያቸው ወደ አቃቤ ህግ ተልኮ በሁሉም ላይ ክስ እንደሚመሰረትባቸውም ፖሊስ አስታውቋል።

በተመሣሳይ መንገድ የተሰማሩ ስደተኞች ካሉ ህዝቡ መረጃ እንዲሰጥ የሻርጃህ ፖሊስ በሚዲያዎች ጥሪ አቅርቧል።

ባለፈው ዓመት በሳዑዲ ዐረቢያ- ሪያድ ውስጥ የገናን በ ዓል ምክንያት በማድረግ ተሰባስበው ሲጸልዩ የነበሩ 35 ኢትዮጵያውያን በሳዑዲ ፖሊስ ለወራት ታስረው ከፍ ያለ ስቃይና መከራ ካሳለፉ በሁዋላ በ ዓለማቀፉ ማህበረሰብ ግፊት ተፈተው ወደ አገራቸው እንዲመለሱ መደረጋቸው ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide