መስከረም ፯ (ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ድርጅቱ የተለያዩ ቀስቃሽ ጽሁፎችን እና መግለጫዎችን በተለያዩ የአዲስ አበባ አካባቢዎች መበተኑ ታውቋል።
ድርጅቱ ” የአንባገነኑ ስርአት በየቤተ እምነቱ ውስጥ ጣልቃ እየገባ የአማኞቹን ሰላም እየነሳ እንደሚገኝ፣ ዘረኛው ስርአት ሀገሪቷን በዘር ከፋፍሎ አንዱን ብሄር ከሌላኛው ጋር በማጋጨት የህዝቡን የመኖር ህልውና አስጊ ደረጃ ላይ ማድረሱን ፣ በአገዛዙ ቅጥረኞች የአማራውን ህዝብ ከደቡብ ክልል ማባረሩን፣የኦሮሞን፣የአፋርን፣ የጋንቤላን፣ የሱማሌን እንዲሁም ሌላውንም ኢትዮጵያዊ በልማት ስም ከቦታው እያፈናቀለ እንደሚገኝ ፤ለም መሬታችንን ለባእዳን አሳልፎ እንደሚሰጥ፣ የተቃዋሚ ፖለቲካ ድርጅቶች መሪዎችን እና አባሎቻቸውን ማስፈራራት፣ማሰቃየት፣ማዋከብ፣ ማሰር እንዲሁም በነጻ ጋዜጠኞች ላይ እስር፣እንግልት፣ማሰደድ፣በማስፋራራት ከስራቸው እንዲርቁ ማድረጉን ” መቀጠሉን የሚያትት ጽሁፍ በትነዋል።
በተበተነው የድርጅቱ መግለጫ ላይ “የመንግስትን እኩይ ተግባር በማወቅም ሆነ ባለማወቅ የምትፈጽሙም ሆነ የምታስፈጽሙ ድርጅቶች፣ግለሰቦች፣የአገዛዙ የፖሊስ፣የደህንነት፣የመከላከያ ሰራዊት፣የቀበሌና ወረዳ ባለስልጣን ሌሎቹም ጭምር ይህን እኩይ ተግባራችሁን ባስቸኳይ በማቆም ወደ ህዝብ ትግል በማንኛውም መንገድ በመቀላቀል ከህዝብ ጎን በመቆም የበደላችሁትን ህዝብና አገር ግዜው ሳያልፍ በመካስ ከታሪክ ተወቃሽነትና ከህዝብ ቁጣ እራሳችሁን ታድኑ ዘንድ እና ለማይቀረው ለውጥ አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ እንጠይቃለን” የሚል ይዘት መኖሩንም ለማወቅ ተችሎአል።
ድርጅቱ በአዲስ አበባ ተመሳሳይ የቅስቀሳ ወረቀቶችን ሲበትን አሁን ለአራተኛ ጊዜው ነው።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide