ግንቦት 7 በተለያዩ አገራት የሚያደርጋቸው ስብሰባዎች በተሳካ ሁኔታ መካሄዳቸውን ታወቀ

ነሃሴ ፳፮(ሃያስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ አቶ አንዳርጋቸው ጽጌን በኢትዮጵያ የደህንነት ሃይሎች ታፍኖ መወሰድ ተከትሎ

ንቅናቄው በተለያዩ አገራት የጠራው ህዝባዊ ስብሰባ በተሳካ ሁኔታ መጠናቀቁን ዘጋቢዎቻችን ገልጸዋል፡

በኖርዌይ በተካሄደው ስብሰባ 250 ሺ የሚጠጋ ክሮነር ሲዋጣ፣ ዝግጀቱም በደመቀ ሁኔታ መጠናቀቁን ባልደረባችን አበበ ደመቀ ተናግሯል። በስብሰባው

ላይ እንግዳ የነበሩት የንቅናቄው የህዝባዊ እምቢተንነት ሊ/መንበር አቶ አበበ ቦጋለ ግንቦት7 አሁን ያለበትን ደረጃ ለተሰብሳቢው ሲገልጹ፣ በቅርቡ ውህደት

ለመጀመር ስምምነት የተፈራረሙት የአርበኞች ግንባር፣ የአማራ ዲሞክራሲያዊ ንቅናቄና የግንቦት 7 ህዝባዊ ሃይል ተወካዮች ንግግር አድርገዋል።

የጀርመን ከተሞች በሆኑት ሙኒክና ፍራንክፍርትም ተመሳሳይ ዝግጅት መካሄዱን የጀርመን ዘጋቢ፣ ሃይሉ ማሞ ገልጿል።