ጋዜጠኛ አልያስ ገብሩ የዋስትና መብት ተከለከለ

ግንቦት ፲፱(አስራ ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የእንቁመጽሔት ዋና አዘጋጅ ጋዜጠኛ ኤልያስ ገብሩ በጅማ ዩኒቨርስቲ ለተነሳው የተማሪዎች ተቃውሞ በመጽሄቱ ላይ የወጣ ጽሁፍ ምክንያት ሆኗል በሚል ተከሶ የ7 ቀናት የጊዜ ቀጠሮ ተጠይቆበት ወደ እስር ቤት ተመልሷል።

አዘጋጅኤልያስገብሩህገመንግስታዊ መብቱን በመጠቀም ከውጭ የመጣውን ጽሁፍ ማስተናገዱን ገልጾ ዋስትና እንዲፈቀድለት ቢገልጽም፣ ፍርድ ቤቱ ግን ያውስትና መብቱን ጥያቄ ሳይቀበለው ቀርቷል ፡፡

ዳኛው “ክሱ የዋስትና መብት ባያስከለክልም የሚጣራ ነገር ስላለ የተጠየቀው የጊዜ ተፈቅዷል ብለዋል።