መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የአገሪቱ የመከላከያ ሚኒሰትር ጆን ኑዩዎን እንደገለጡት በአዲስ አበባ በተፈረመው ስምምነት መሰረት፣ ደቡብ ሱዳን ጦሩን ሙሉ በሙሉ ከአወዛጋቢው የድንበር አካባቢ ብታወጣም ሰሜን ሱዳን ግን ጦሩዋን እስካሁን አላንቀሳቀሰችም።
ሚኒሰትሩ በአካባቢው የሰፈረው የተመድ የሰላም አስከባሪ ሀይል ሱዳን ጦሩዋን ለምን እንዳለስወጣች መጠየቅ አለበት ብለዋል።
በሁለቱ አገሮች መካከል የተነሳው ውዝግብ ከዛሬ ነገ መቋጫ ያገኛል ተብሎ ቢጠበቅም እስካሁን መፍትሄ አላገኘም።