የኢትዮጵያ ጦር ከሶማሊያ ለቆ ሊወጣ ነው

መጋቢት ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም 

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ ጦር ሰሞኑን ሁድሩ ከምትባለዋ የሶማሊያ ከተማ መልቀቁን ተከትሎ ባይደዋንና ሌሎች አካባቢዎችን በመተው ሙሉ በሙሉ ከሶማሊያ ሊወጣ ይችላል የሚለው መላምት አይሏል።

የአፍሪካ ህብረት የሰላም አስከባሪ ሀይል የኢትዮጵያ ጦር አገሪቱን ለቆ ከወጣ የአልሸባብን ጦር ለመቋቋም እንደማይችል እየተነገረ ነው። የህብረቱ የሰላም አስከባሪ ሀይል አዛዥ የሆኑት አንድሪው ጉቲ ህብረቱ ሀይሉን እየገመገመ መሆኑን ተናግረዋል።

አልሸባብ የኢትዮጵያ ጦር  ሁድሩን መልቀቁን ተከትሎ ወዲያውኑ ከተማዋን ተቆጣጥሯል። ከኢትዮጵያ ጦር ጋር እጅና ጓንት በመሆን ሲሰሩ የነበሩ ሶማሊዎች ፣ የኢትዮጵያ ጦር አገሪቱን ለቆ ይወጣል የሚለውን ዜና እንደሰሙ ወደ መሀል አገር እየተሰደዱ ነው።

ላለፉት 2 አመታት በሶማሊያ የቆየው የኢትዮጵያ ጦር አልሸባብን ሙሉ በሙሉ ማጥፋት ሳይችል ቀርቷል።