ደቡብ ሱዳንን እና ሰሜን ሱዳንን ለመሸምገል የተያዘው ቀጠሮ ተሰረዘ

መጋቢት 17 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- በሚቀጥለው ሳምንት በቅርቡ ነጻ የወጣችውን ደቡብ ሱዳን እና ሰሜን ሱዳንን ለመሸመግለን በአዲስ አበባ ተይዞ የነበረው ቀጠሮ የተራዘመው ሁለቱ አገሮች ተመልሰው ወደ ጦርነት በመግባታቸው ነው።
አለማቀፍ የመገናኛ ብዙሀን እንደገለጡት በሁለቱ አገሮች ድንበሮች መካከል ጦርነት እየተካሄ ነው። የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት ጦርነቱን የጀመረው የሰሜን ሱዳን መንግስት ነው ያለ ሲሆን የሰሜን ሱዳን መንግስት በበኩሉ ጦርነቱን የጀመሩት ደቡቦች ናቸው ይላሉ።
ሁለቱ አገሮች ጦርነት ላለማካሄድ በቅርቡ አዲስ ስምምነት መፈራራማቸው ይታወሳል። ይሁን እንጅ የደቡብ ሱዳን ባለስልጣናት በሰሜን ሱዳን ላይ የጣሉትን የነዳጅ ማእቀብ ለማንሳት ፈቃደኛ ባለመሆናቸው በሁለቱ አገሮች መካከል ጦርነት ሊነሳ ይችላል የሚለው ግምት በብዛት ሲሰጥ ቆይቷል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ጸሀፊ የሆኑት ባንኪ ሙን ሁለቱ አገሮች ጦርነቱን አቁመው ወደ ውይይት እንዲያመሩ ጠይቀዋል።