የግል ፕሬስ አሳታሚዎች ማተሚያ ቤቶች ያቀረቡትን አዲስ ውል በመቃወም መግለጫ አወጡ

ሚያዚያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም  

ኢሳት ዜና:-ጋዜጦችና መጽሔቶችን  የሚያትሙት  ማተሚያ ቤቶች ለግል ጋዜጦችና  መጽሔቶች  አሳታሚዎች  የላኩት የሕትመት ውል ቅድመ ምርመራን (Censorship) አንግሶ  ሕገ መንግሥቱንና  የፕሬስ ነፃነትን  የሚፃረር  ነው  ሲሉ አሣታሚዎች  ተቃውመውታል፡፡ አቤቱታቸውንም ለአቶ  መለስ ዜናዊና  ለአታሚዎቹ  በዛሬው ዕለት አቅርበዋል፡፡  አሳታሚዎቹ የሕትመት “ስታንዳርድ” ውል ረቂቅ አዋጅ  ቅጂ ከደረሳቸው በኋላ በተናጠል ሳይሆን በጋራ አቋም ለመያዝ በተደጋጋሚተሰብስበዋል፡፡ በስብሰባቸውም  ላይ  እንደዚህ  ዓይነት ውል እንዲፈርሙ የተላከው ከብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት፣ ከቦሌ ማተሚያ ቤትና ከሌሎችም መሆኑን ተገንዝበዋል፡፡

ለአቶ መለስ ባቀረቡት የአቤቱታ ደብዳቤ በሌሎች ማተሚያ ቤቶች የሚያሳትሙ አሳታሚዎችም በጋራ ያሉበት ሲሆን፤ በብርሃንና ሰላምማተሚያ ድርጅት የተላከው ግን እዚያው በሚያሳትሙ አሳታሚዎች ነው፡፡

አሳታሚዎቹበወሰዱት አቋም እንዲፈርሙ ከተላከላቸው የውል ረቂቅ ውስጥ እጅግ ያሳሰባቸው አንቀፅ 10 ላይ የሰፈሩት ሀሳቦች ናቸው፡፡ አንቀጽ10 ሕግን የተላለፈ ይዘትን አለማተም 10.1 አታሚው በአሳታሚው እንዲታተም የቀረበለት የጽሑፍ ስክሪፕት ሕግን የሚተላለፍስለመሆኑ ለማመን በቂ ምክንያት ካለው አላትምም የማለት መብት አለው እንዲሁም  አንቀጽ 10.2 አታሚው አሳታሚው የሕግ ተጠያቂነትን የሚያስከትል የሕትመት ይዘት የማውጣት ዝንባሌያለው መሆኑን ለማመን በቂ ምክንያት ካለው በማንኛውም ጊዜ ውሉን ለማቋረጥ ወይም ለመሰረዝ ይችላል የሚሉ ድንጋጌዎችን ይዘዋል።

እነዚህበአንቀፁ የሰፈሩት ኀሳቦች በሕገ መንግሥቱ አንቀፅ 29 ላይ ቅድመ ምርመራ በማናቸውም ሁኔታ የተከለከለ ነው የሚለውን የሚፃረር በመሆኑ ውሉን መፈረም መንግሥቱን በመፃረር ቅድመ ምርመራን መቀበል ነው ብለው በማመን ድርጊቱን በጥብቅ ተቃውመዋል፡፡ አሳታሚዎቹ ከውሉ ቅድመ ምርመራ ይዘት በተጨማሪ የብርሃንና ሰላም ማተሚያ ድርጅት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ቀጠሮ ከተያዘ በኋላ ስብሰባውን ወደ ጎን በመተው ሁለት ሳምንት ሙሉ በስልክና በደብዳቤ “መጥታችሁ ካልፈረማችሁ የሕትመት ውጤታችሁ አይታተምም”በማለቱ በአሳታሚዎቹ ዘንድ ከፍተኛ ቅሬታና ትዝብት አስከትሏል፡፡

አሳታሚዎቹ ባደረጉት ስብሰባ ችግር ሲኖር ከመሰብሰብ ይልቅ ቋሚ የሆነ የአሳታሚዎች ማኅበር የመመሥረትን አስፈላጊነት በማመን የምሥረታእንቅስቃሴው እንዲጀመር ወስነዋል፡፡ በተጨማሪም በቅድመ  ምርመራ መልክ የመጣውን የውል ረቂቅ አሳታሚዎች ቢቃወሙትም ሚዲያውም ራሱ ከሕግ ጥሰትና ከሥነ ምግባር ጉድለት መታቀብናመጠንቀቅ እንዳለበት ያምናል፡፡ ሚዲያው የራሱን ጉድለት በማየትና በሕዝብ የሚቀርብለትን አቤቱታ እያስተናገደ እንዲያስተካክልና እንዲጠናከር ለማድረግ የተጀመረው የሚዲያ ጉባኤ “ካውንስል” ምሥረታ ሂደት ባስቸኳይ ተጠናቆ ጉባኤው እውን እንዲሆን ወስኗል፡፡ በአሁኑ ጊዜ የፕሬስ ውጤቶች እየደረሰባቸው ያለው አደጋ የራሳቸው ማተሚያ ቤት ስለሌላቸውና አብዛኞቹ በመንግሥት ማተሚያ ቤት ስለሚያሳትሙት ነው፡፡ አሳታሚዎቹም ይህንን በመረዳት ለወደፊቱ በጋራ ተጋግዘውና ተደጋግፈው የጋራ ማተሚያ ቤት ለማቋቋምተስማምተዋል፡፡

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide