ሰኔ ፲፱ (አስራ ዘጠኝ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ድርጅት በሁሉም ጣቢያዎቹ ይሰሩ የነበሩ ከ500 በላይ ሠራተኞችን ከስራ ማባረሩን ለማወቅ ተችሎአል፡፡
ድርጅቱ ሰራተኞችን ከሰኔ 17 ጀምሮ ያሰናበተ ሲሆን፣ ሰራተኞች አስቀድሞ ያልተነገራቸው በመሆኑና ያለአንዳች ካሳ በመባረራቸው ለከፍተኛ የኢኮኖሚና የስነልቦና ችግር ተዳርገዋል።
ድርጅቱ በሁመራ በቡሬ እና ከ100 በላይ በሚሆኑ ሌሎች ጣቢያዎች የሚገኙ ሰራተኞችም ማበረሩን ስማቸው እንዳይገለጽ የጠየቁ የድርጅቱ ሰራተኞች ገልጸዋል።
በጉዳዩ ዙሪያ የምርት ገበያ ድርጅት ሀላፊዎችን ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።