ኢሳት (ታህሳስ 13 ፣ 2008)
በኦሮሚያ ክልል ከተሞች የተቀሰቀሰውን ተቃውሞ ተከትሎ በኦሮሚያ ሬድዮና ቴሌቪዥን ድርጀት ውስጥ የሚሰራ ጋዜጠኛ ለእስር ማዳረጉ CPJ ገለጠ
የጋዜጠኛ መብት ተሟጋች ድርጅቱ ጋዜጠኛው ፍቃዱ ምርካና ቅዳሜ ጠዋት አዲስ አበባ ከተማ ከሚገኘው መኖሪያ ቤቱ በጸጥታ ሀይሎች መታሰሩን አስታውቋል ።
ጋዜጠኛው የታሰረበት ምክንያት በግልጽ አለመታወቁን ያስታወቀው ድርጅቱ መንግስት ጋዜጠኛውን በአስቸኳይ እንዲፈታ ጠይቋል ።
ለደህንነታቸው ሲሉ ማንነታቸውን ከመግለጽ የተቆጠቡ እማኞች ጋዜጠኛ ፍቃዱ የታሰረበት ቦታ እስካሁን እንደማይታወቅና ቤተሰቡም ሆነ ጠበቃ ለመጎብኘት ፈቃድ እንዳላገኙ ለጋዜጠኛ መብት ተሟጋች ተቋሙ አስረድቷል ።
ድርጀቱ በጋዜጠኛው መታሰር ዙሪያ ከመንግስት ሆነ ኬንያ ከሚገኘው ኤምባሲ መረጃን ለማግኘት ያደረገው ጥረት እንዳልተሳካለትም አክሎ አስታውቋል።
ባለፈው አመት ከአዲስ አበባ ማስተር ፕላን ጋር በተገናኘ ተቀስቅሶ ከነበረው ግጭት ጋር በርካታ የኦሮሚያ ሬዲዮና ቴሌቭዥን ጋዜጠኞች ለእስር መዳረጋቸውና መታገዳቸው የታወሳል ።
የጋዜጠኞችንና የተቃዋሚ ሀይሎችን ለማፈን እየተጥቀሙበት እንደሚገኝ CPJ አክሎ ገልጿል።