አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር ህክምና እንዳያገኙ ተከለከሉ

ታኀሳስ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፰ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ ፕሬዝደንት አቶ ዘሪሁን ገ/እግዚያብሄር የህክምና አገልግሎት እንዳያገኙ መደረጋቸውን ነገረ ኢትዮጵያ ቤተሰቦቹን ጠቅሶ ዘግባል፡፡
አቶ ዘሪሁን በማዕከላዊ እስር ቤት በደረሰባቸው ድብደባ እጃቸው፣ እግራቸውና ጆሮአቸው ላይ ጉዳት የደረሰባቸው ቢሆንም ህክምና እንዳያገኙ ተከልክለዋል። አቶ ዘሪሁን በማዕከላዊ እስር ቤት እጃቸው የፊጥኝ ታስረውና ተንጠልጥለው በተገረፉበት ወቅት የግራ እጅ አጥንታቸው የተሰበረ ሲሆን የእግር ጥፍሮቻቸውም ተነቅለዋል፡፡
የ17 አመት ፍርደኛ የሆኑትና በዝዋይ እስር ቤት የታሰሩት አቶ ዘሪሁን በአሁኑ ወቅት ለህክምና ቃሊቲ የሚገኙ ቢሆንም አሁንም ህክምና እንዳላገኙ ቤተቦቹ ለጋዜጣው ተናግረዋል፡፡