የካቲት ፩ (አንድ) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በሳውዲ አረቢያ ሪያድ የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ለ አባይ ግድብ ማሰሪያ የሚውል የቦንድ ግዥ የሚካሄድበትን ፕሮግራም የያዘው ከሳምንታት በፊት ነው።
በፕሮግራሙ መሰረት ትናንት ሐሙስ ከወትሮው በተለዬ መልኩ በሪያድና አካባቢው የሞኖሩ በርካታ ኢትዮጵያውያን በስፍራው በመገኘት የኮሙኒቲውን አዳራሽ ከ አፍ እስከ ገደፉ ይሞሉታል።
የቦንድ ግዥውን ፕሮግራም ለመምራት ወደዚያው ያቀኑት የኢህአዴግ ባለስልጣናትም በስብሰባው ከተገኘው በርካታ ሰውደጎስ ያለ ገንዘብ እንደሚያሰባስቡ ተስፋ ያደረጉ።
ሆኖም ሰሞኑን<<ጂሀዳዊ ሀረካት”በሚል ርዕስ መንግስት በ እስር ላይ ያሉትን የሙስሊም መፍትሔ አፈላላጊ ኮሚቴዎች አስመልክቶ በቴሌቪዥኑ በለቀቀው ፊልም ቁጣቸው እየተቀጣጠለ በ አዳራሹ የተገኙት ሙስሊሞች የቦንድ ግዥውን ስብሰባ ወደ ከፍተኛ የተቃውሞ ትዕይንት ቀይረውታል።
“ግድቡ ከመሪዎቻችን መፈታትና ከሰላማችን በሁዋላ ይደርሳል”በማለት ቅሬታቸውን መግለጽ የጀመሩት በሪያድ የሚኖሩ ሙስሊሞች፤ <<ኢቲቪ ሌባ!ኢቲቪ አሸባሪ!መጂሊስ ይውረድ! መሪዎቻችን ይፈቱ!ድምፃችን ይሰማ!>>በማለት አዳራሹንና አካባቢውን በከፍተኛ ጩኸት አናውጠውታል።
ገንዘብ ለማሰባሰብ ወደ ፕሮግራሙ የመጡት የ ኢህአዴግ ባለስጣናትም ሁኔታቸው ከቁጥጥር ውጪ በመሆኑ በከፍተኛ ድንጋጤ በመጡበት አኳሁዋን መመለሳቸው ታውቋል።
በ ሳውዲ አረቢያ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በቅርቡ መንግስት በህዝበ ሙስሊሙ ላይ እየፈጸመ ያለውን ግፍ እና በደል በመቃወም ለመንግስት ተደጋጋሚ የተቃውሞ ደብዳቤ ማስገባታቸው ይታወሳል።