የኢህአዴግ መንግሥት በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጽ/ቤት (መጅሊስ) ምትክ የሚመረጠው አዲሱ መጅሊስ በቀበሌና በወረዳ በካድሬዎች ለማካሄድ በዝግጅት ላይ ነው ተባለ

ግንቦት ፴ (ሰላሳ) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የዑላማዎች ምክር ቤት በበላይነት ይመራዋል በተባለው የመጅሊስ ምርጫ በቀበሌና በወረዳ በመንግሥት መዋቅር የሚካሄድ ሲሆን የፌዴራል ጉዳዮች ጽ/ቤት በሚመድበው ቀጥተኛ በጀት ደግሞ ከሰኔ 13 እስከ ሰኔ 15 ቀን 2004 ዓ.ም የክልሎች የእስልምና ምክር ቤት (መጅሊስ) ይመረጣል።   ሰኔ 30 ቀን 2004 ዓ.ም ደግሞ የአዲስ አበባ እስልምና ምክር ቤት ምርጫ ይካሄዳል የሚል መርሃ- ግብር በመንግሥት በኩል ወጥቶ ለኢህአዴግ ሙስሊም ካድሬዎችና በመፍረስ ላይ ላለው የመጅሊስ ባለስልጣናት ተሰጥቷል ተብሎአል፡፡

ይህ በእንዲህ እንዳለ የሙስሊሙ ማህበረሰብ መብቱን ለማስከበር የመረጣቸው 17 ጊዜያዊ የኮሚቴ አባላት ምርጫው በቀበሌ ሳይሆን በመስኪድ፣ በመንግሥት ካድሬ የዑላማዎች ምክር ቤት ሳይሆን በህዝበ ሙስሊሙ መካሄድ አለበት ብለው ከፌዴራል ጉዳዮች ሚንስትር ጋር የተከራከሩ ሲሆን በመጪው ዓርብ ለህዝበ ሙስሊሙ አቋማቸውን በመስኪድ ይፋ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide