ህዳር ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ገበሬዎቹ ተቃውሞአቸውን የገለጹት የወተት ወጋ በመውደቁ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ ገበሬዎች ፣ በርካታ ትራክተሮችን በማሰልፍ የቤልጂም ዋና ከተማ በሆነችው ብራሰልስ ተመዋል።
የወተት ወጋ 25 በመቶ እንዲጨምር የጠየቁት ገበሬዎቹ የአውሮፓ ህብረት ህንጻዎችን በወተት በመርጨት ነጭ አድረገዋቸዋል።
የአውሮፓ ገበሬዎች ገበያው ሊሸከመው ከሚችለው በላይ የወተት ምርት የሚያመርቱ በመሆኑ ህብረቱ በየአመቱ ከ47 ቢሊዮን ዩሮ በላይ በማውጣት ለመደጎም ተገዷል።