የአካል ጉዳተኞች የኤች አይ ቪ ኤድስ አገልግሎቶች ተጠቃሚ እንዳልሆኑ ተገለፀ

የካቲት 30 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በኤች አይ ቪ ኤድስ ላይ የሚደረጉ ዘመቻዎችና ቅስቀሳዎችን ለማካሄድ በስራ ላይ የሚዉሉት የመገናኛ ስልቶች የአካል ጉዳተኞችን ግምት ዉስጥ ያላስገቡ በመሆናቸዉ በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞች ለበሽታዉ ያላቸዉ ግንዛቤ ዝቅተኛ ከመሆኑም በላይ ከበሽታዉ ጋር የተያያዙ አግልግሎቶችን ሊያገኙ እንደማይችሉ አንድ የረድኤት ድርጅት የስራ ሃላፊ ገለፁ። 

ሊያ ሰሎሞን በኢትዮጵያ የአካል ጉዳተኞችና ልማት ማእከል the Ethiopian Centre for Disability and Development (ECDD) የቤተሰብ መምሪያና የተዋልዶ ጤና አገልግሎት ፕሮጀክት አስተባባሪ በየጤና መስጫዉ ከአካላዊ እንቅስቃሴ እስከ በሽታዉ የምክር አገልግሎትና ምርመራ ድረስ ለአካል ጉዳተኞች የሚሰጠዉ አገልግሎት ዝቅተኛ እንደሆነ ገልፀዋል።

የአዲስ አበባ ጤና ቢሮ በዚህ ረገድ መጠነኛ መሻሻል መደረጉን በማመን የተደረገዉ መሻሻል በተገቢዉ አቅጣጫ ለመጓዝ አንድ እርምጃ ቢሆንም እዉነተኛ መፍትሄ ለመስጠት ግን የአካል ጉዳተኞችን አጀንዳ የመንግስት ፖሊሲዎች አካል ተደርጎ በሁሉም መስክ መወሰድ እንዳለበት መጠቆሙን አይሪን የዜና ወኪል ገልጿል።  

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide