ጥር 14 ቀን 2004 ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- ብሎጉ እንደዘገበው ፤ሰሞኑን የመከላከያ ኢንጄነሪንግ ኮሌጅ ሲቪል ሰራተኞች በግዴታ እረፍት እንዲወስዱ ታዘዋል።
ብሎጉ በማያያዝም፦”ለተለያዩ የኮሌጁ ሰራተኞችም የደሞዝ ጭማሪ ተደርጎላቸዋል። እንዲህ አይነት ሁኔታዎች የሚከሰቱት አገሪቱ ለጦርነት ስትዘጋጅ ነው”ሲል ምንጮቹን ጠቅሶ ዘግቧል።
በሌላ በኩል መንግስት አንዳንድ የአዲስ አበባ የቀበሌ ነዋሪዎችን ኤርትራ በወሰደችው እርምጃ ዙሪያ እያወያየ ነው።
የአፋር ህዝብ ባወጣው መግለጫ ደግሞ መንግስት ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሁዋላ የተዘጉትን የዱብቲ፣ ሳማራ፣ ዲኮቶና ማንዳ ሆስፒታሎችን መልሶ በመክፈት 200 የሚሆኑ ነርሶችን አሰማርቷል።
የቀድሞ ወታደሮችና አሁን በአገልግሎት ላይ ያሉት ጭምር፤ የደሞዝ ጭማሪ እየተደረገላቸው መሆኑም ተመልክቷል።
የአማራ ክልል የ ኢሳት ወኪል ግን፣ መንግስት የኤርትራን መንግስት የሚያወግዝ ተደጋጋሚ ፕሮፓጋንዳ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን እያካሄደ ቢሆንም፣ ከወትሮው የተለየ ወታደራዊ እንቅስቃሴ እስካሁን በአካባቢው እንዳልታየ ገልጿል።