ጥር ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ የጸረ ሙስና ኮሙሽን አቃቢህግ ሙስና ተፈጽሞበታል በማለት ክስ በመሰረተበትና ውሳኔ በተላለፈበት አለምአቀፍ ጨረታ ጉዳይ ላይ የአለም ባንክ ባለሙያዎች ምርመራ ማድረግ መጀመራቸው ተገለጠ::
ከሶስት ሳምንት በፊትም ሁለት የአለም ባንክ ባለሙያዎች በዚህ ጉዳይ ላይ የመንግስት ባለስልጣናት ማነጋገራቸው ይታወቃል::
አዲስ ፎርቹን ጋዜጣ ከአዲስ አበባ እንደዘገበው የገጠር የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት ዙሪያ በግዥና ሽያጭ ተፈጸመ የተባለው ሙስና በግዥና ሽያጭ ኮሚቴ ጸሀፊው አቶ ብርሀኑ ሂካ 4 500 ዩሮ ከጨረታ ተሳታፊ የጀርመን ኩባኒያ ተቀብለው የለአግባብ ለመበልጸግ ሞክረዋል በሚል በፍርድ ቤት የ 3 አመት የእስር ቅጣት ተጥሎባቸዋል::
ኢትዮጵያ ከአለም ባንክ ከምታገኘው የአለም አቀፍ የኤሌክትሪክ አክሰስ ፕሮጀክት አካል የሆነው ይህሮፕት ከተያዘለት 200 ሚሊዮን ዶላር ውስጥ ሙስና ተፈጸመበት የተባለው የኤሌክትሪክ ፕሮጀክት 30 ሚሊዮን ዶላር መሆኑንም ለማወቅ ተችሎል::
በፎርቹን ዘገባ መሰረት የአለም ባንክ የስነ ምግባር ባለሙያዎች በህግ ባለእዳው አቶ ብርሀኑ ሂካ በ3 አመት እስር ከመቀጣታቸው በላይ ለበላይ ፍርድ ቤት ያቀረቡት ይግባኝ ተቀባይነት እንዳላገኝ ለማወቅ ተችሎል::
ይህንን ጉዳይ ለማጣራት ነው የአለም ባንክ ባለሙያዎች ምርመራ ጀመሩ የተባለው::
በዚህ የ30 ሚልዮን ብር ጨረታ በርካታ አለም አቀፍ ተጫራቾች ተሳትፈው እንደነበርም ተዘግቦል::