ከፍተኛ ድብደባ የተፈጸመባት ወይዘሪት ወይንሸት ሞላ በድጋሜ ተቀጠረች

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለፈው አርብ የኢህአዴግ የጸጥታ ሃይሎች በሙስሊም ኢትዮጵያውያውያን ላይ ያደረሱትን ኢ ሰበአዊ እርምጃ ተከትሎ በአካባቢው

ስትንቀሳቀስ ተገንታለች በሚል ሰበብ የተያዘቸው የሰማያዊፓርቲብሄራዊምክርቤትናየሴቶችጉዳይአባልወይዘሪትወይንሸትሞላለሐምሌ 24 ቀን 2006 ዓ.ም በድጋሜ ተቀጠራለች፡፡

ወይንሸትጭንቅላቷ አካባቢ የተመታች ሲሆንእጇም በፋሻ እንደታሰረበስፍራው የነበሩ ጓደኞቿ ለኢሳት ገልጸዋል።

ችሎቱን ለመከታተል ወደ ፍርድ ቤት ካቀኑት የሰማያዊ ፓርቲ አባላት መካከል አቤልኤፍሬም በፖሊሶች መወሰዱ ታውቋል።

ችሎቱን ለመከተታል የተገኘችው የሰማያዊ ፓርቲ አባል የሆነችው እየሩሳሌም ተስፋው፣ ፖሊሶቹ ችሎቱን ለመከታተል በተገኙት ሰዎች ላይ ይናገሩ የነበሩት ንግግር ” ከፖሊስ የማይጠበቅ”

መሆኑን ተናግራለች።

ኢህአዴግ እያወሰደ ያለው እርምጃ፣ አገዛዙ የመጨረሻ እድሜው ላይ መገኘቱን እንደሚያሳይም አክላ ገልጻለች