በእስራኤል የሚኖሩ ወጣቶች ለኢሳት የገንዘብ ድጋፍ አደረጉ

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በእስራኤል ኦር ይሁዳ የሚኖሩ ጓደኛሞች በራስ ተነሳሽነት ተሰባስበው ለኢሳት ያሰባሰቡትን ከ6 ሺ ዩሮ በላይ ገንዘብ አስገብተዋል።

ገንዘቡን በማሰባሰብ በኩል ከፍተኛ ሚና የተጫወተው በየነ ቀጸላ ፣  በልጁ በእዮብ አንደኛ አመት የልደት ቀን ኢሳትን የመርዳት ሃሳብ እንደመጣለትና በበአሉ ላይ የተገኙት ጓደኞቹ ከፍተኛ

የገንዘብ አስተዋጽኦ ማድረጋቸውን ገልጿል።

ኢሳት በአገራችን ስላለው ሁኔታ ቤተእስራኤላውያን እና በእስራኤል የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን መረጃ እንዲያገኙ መርዳቱን የገለጸው በየነ፣ ለወደፊቱም ተመሳሳይ ድጋፍ ለማድረግ እንደሚሰሩ ቃል ገብቷል።

በየነ እና ጓደኞቹ ያደረጉት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የሚደነቅና ለሌሎችም ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን የገለጸው የኢሳት ማኔጅመንት፣ የልደት በአሉን ለካበረው ለእዮብ በየነም መልካም ዘመን ፣

ለበየነና ጓደኞቹም ምስጋናውን አቅርቧል።