የጎንደር ህዝብ ከከፍተኛ አስተዳደራዊ ችግር አለብን ሲል በከተማው ለተገኙት አቶ ሃማርያም ደሳለኝ ተናገረ

ሐምሌ ፲፯(አስራ ሰባት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከሳምንታት በፊት በጎንደር ዩኒቨርስቲ የምረቃ ስነስርአት ላይ የተገኙት አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ ከከተማውና ከአካባቢው ህዝብ ተወካዮች

ጋር ባደረጉት ውይይት፣ ህዝቡ በድፍረት ያሉበትን የመልካም አስተዳደርና ልማት ችግሮች ዘርዝሮ አቅርቧል።

አንድ አስተያየት ሰጪ፣ “ከጎንደር አየር ማረፊያ እስከ አዘዞ ያለው መንገድ እናንተ ትማጣላችሁ ተብሎ በአፈር ተደለደለ እንጅ መኪና አያሳልፍም ነበር” ብለዋል። “ውሃንም በተመለከተ አላህ አልፎ አልፎ

ዝናብ እያዘነበልን ነው እንጅ አንገረብን የመሰለ ውሃ እያለ በውሃ ጥም እናልቅ ነበር፣ ግማሹን ማህጸነ ሰፊ ግማሹን ማህጸነ ጠባብ እያደረጉት ነው ” በማለት  አስተያየት ሰጪው አክለዋል

አንድ ከበየዳ ወረዳ የመጡ ሰው ደግሞ ወረዳው መብራት እንዳልገባለት ፣ በየአመቱ በርካታ የመንግስት ሰራተኞች እየፈለሱ መሆኑን በያዝነው አመት ብቻ 141 መምህራን ከወረዳው መፍለሱን ተናግረዋል።

ወጣቶች መሬት በማጣታቸው ማህበራዊ ችግሮች እየተፈጠሩ መሆኑን ግልጸዋል

በጎንደር ከፍተኛ የመንገድ ችግር እንዳለ የገለጹት አንዲት ተናጋሪ ፣ በከተማው ስላለው ውሃ ሲናገሩ ደግሞ ” ምግብ በልተን ውሃ መጠጣት የማችልበት ደረጃ ደርሰናል” ብለዋል። “ጎንደር ተረስታለች” ያሉት ተናጋሪዋ

በከተማዋ የመልካም አስተዳደር ችግር አለ ሲሉ አክለዋል።

አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝ የመስራት ፍላጎት ቢኖርም አቅም አለመኖሩን ፣ አቅምም ቢኖር የአመለካከትና የአፈጻጸም ችግር መኖሩን ተናግረዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ በሞያሌ ከተማ ውሃ ከጠፋ 1 ወር መሙላቱን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። በደብረማርቆስ ከተማ ደግሞ ከፍተኛ የሆነ የስኳር እጥረት ማጋጠሙን ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል።