ከኦሮሚያ ክልል፣ ቡሌሆራ አካበቢ ተፈናቅለው በመጠልያ ጣቢያ የሚኖሩ የቡርጂ ብሔረሰብ አባላት ይትቃወሞ ስለፈ አድርጉ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 09 ቀን 2010 ዓ/ም ) የኢሳት ወኪሎች ከስፍራው ያደረሱን መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ተፈናቃዮቹ በዋነኝነት ሰልፍ የወጡት በመንግስት በኩል ተዘንግተናል በማለት ነው።
ከነቤተሰባችን ችግር ላይ በወደቅንበት ሁኔታ አያለን መንግስት ትኩረት ሊሰጠን ይገባል ያሉት ሰልፈኞቹ ፤በግጭት ምክንያት ከአንድ አመት በላይ የተዘጋው የቡርጂ-ዲላ እና የቡርጂ-ሀገረማርያም መንገድ እንዲከፈት ጠይቀዋል።
የወረዳና የዞን መልሶ ማዋቀር ስራ እንዲሰራም ጥያቄ አቅርበዋል።