መጋቢት ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ከወራት በፊት በአስከፊ ሁኔታ ከሳውድ አረቢያ ወደ ኢትዮጵያ የተመለሱ ዜጎች ተመልሰው እየተሰደዱ እንደሆን መረጃዎች አመለከቱ።
ኢትዮጵያውያውያኑ ስደትን እንደ አማራጭ የሚጠቀሙበት በአገራቸው ለመስራት ሁኔታዎች እንዳልተመቻቹላቸው በመግልጽ ነው።
በተለይ ወደ ትግራይና አማራ ክልሎች እንዲሄዱ የተደረጉ ስደተኞች በሁመራ በኩል ወደ ሱዳን በብዛት እየጎረፉ መሆኑን የአካባቢው ሰዎች ይናገራሉ።
አንዳንድ ወጣቶች ከሳውድ አረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ለቀን ወደ አገራችን ብንገባም በአገራችን የምናየው ነገርም ለስራ የማያበረታታ ነው በማለት አስተያየታቸውን ይሰጣሉ።
ከ130 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያን ከሳውድ አረቢያ እንዲወጡ መደረጉ ይታወሳል። መንግስት በአነስተኛ እና ጥቃቅን እንደሚያደረጃቸው ቃል ቢገባም እስካሁን ይህ ነው የሚባል ውጤት አልተገኘም።