ኢየሱስ በዮርዳኖስ ወንዝ   በዮሐንስ እጅ መጠመቁን ምክንያት በማድረግ በመላው የኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ምእመናን ዘንድ  በየኣመቱ የሚከበረው የጥምቀት በዓል ዘንድሮ  በመላ ሀገሪቱ በድምቀት ተከብሯል።

ጥር ፲፩(አስራ አንድ ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በጎንደር በፋሲል ግንብ አጠገብ በተከበረው በዓለ-ጥምቀት ከትናን የከተራ እለት ጀምሮ በርካታ ቱሪስቶች መገኝታቸውን ወኪላችን ከስፍራው ዘግቧል።

በዓሉ በአዲሰ አበባ ጃን ሜዳም – እንደ ወትሮው ሁሉ እጅግ በደመቀ ሁኔታ መከበሩ ታውቋል። በላሊበላ እጅግ በርካታ ቀሳውስት ተገኝተው በወረብና በዝማሬ ማክበራቸውንም በስፍራው ያለችው ወኪላችን የላከችው መረጃ ያመለክታል።

እንዲሁም በተለያዩ የውጪ ሀገራት የሚገኚ  የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አማኞች  በየሚገኙባቸው ከተሞች በአሉን በመንፈሳዊ ስነ-ስርዓት አክብረውታል።