ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ፎሬን ፖሊሲ መጋዚን ባወጣው የፌልድ ሰቴትስ ኢንዴክስ ኢትዮጵያን ከአለም አገሮች በ17ኛ ደረጃ በማስቀመጥ፣ለአደጋ የተጋለጠች አገር ሲል ፈርጇታል። ለኢትዮጵያ ህልውና አስጊ ሆነው ከቀረቡ ችግሮች መካከል የህዝብ ቁጥር መጨመር፣ የስደተኞች መብዛት፣ የህዝብ ብሶቶች መጨመር፣ ዜጎች አገራቸውን ጥለው መሰደድ፣ የፖለቲካ መሪዎች ልዩነት እና የጸጥታ ሀይሎች ጣልቃ ገብነት የሚሉት ይገኙበታል።
ከሁለት አመት በፊት ኢትዮጵያ እንደ ዘንድሮው ሁሉ በ17 ኛ ደረጃ ላይ ትገኝ የነበረ ሲሆን፣ አምና ግን ደረጃዋን በማሻሻል ወደ 20ኛ ዝቅ ብላ ነበር። በዚህ አመትም በአገሪቱ ውስጥ የሚፈጸመው የሰብአዊ መብቶች ጥሰት መክፋቱን መረጃው ያሳያል። ከአንድ እሰከ 20 ባለው ዝርዝር ውስጥ የሚገኙ አገሮች የመፈራረስ አደጋ ያንዣበበባቸው አገሮች ናቸው። ሶማሊያ አሁንም በቀደማነት ትመራለች። ኤርትራ ከአንድ እስከ 20 ካሉት አገሮች ተርታ በመውጣት በ23 ደረጃ ላይ ትገኛለች።
አዲሱ መረጃ የኢትዮጵያን ማህበራዊ እና ኢኮሚያዊ ችግሮች እያሻሻልኩ፣ አገሪቱን ወደ መካከለኛ ገቢ ለማሳደግ ግስጋሴ ላይ ነኝ ለሚለው የመለስ መንግስት የሚያቀርበውን ተደጋጋሚ ፕሮፓጋንዳ የሚቃረን ነው። የኢትዮጵያ ህለውና ከጊዜ ወደ ጊዜ አደጋ ውስጥ መውደቁን አለመቃፉ የግጭቶች አስወጋጅ ድርጅት ባወጣው ሪፖርት መግለጹ ይታወሳል። በቅርቡ አሜሪካ መንግስት ስቴት ዲፓርትመንትም ለኢትዮጵያ ህለውና አደገኛ የሆኑ የሰብአዊ መብቶች ጥሰቶችና እና የጎሳ ግጭቶችን በዝርዝር አቅርቧል።
___________________________________________________________________________________________________________________________________________________
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide