የካቲት ፬ (አራት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ቅዳሜ እንደ ፈረንጆቹ አቆጣጠር ፌብርዋሪ 9፣ 2013 ከሰዓት በኋላ ጀምሮ እስከ እኩለ ለሊት በስዊድን ዋና ከተማ ስቶክሆልም በተካሄድው የኢሳት የገንዘብ ማሰባሰባቢያ ዝግጅት ላይ ከጨረታ ከመቶ ሰላሳ ሺህ የስዊድን ክሮነር ወይም ከሃያ ሺህ በላይ የአሜሪካን ዶላር ተሰበሰበ።
ይህንን ያህል መጠን ያለው ገንዘብ የተገኘው በዝግጅቱ ላይ የታላቁ ኢትዮጵያዊ የኦርቶዶክስ ቤ/ክ ፓትሪያክ እና የጸረ ፋሽስት ታጋይ እና መስዋእት የነበሩት የአቡነ ጴጥሮስ ምስል ለጨረታ ቀርቦ ከተሸጠ በኋላ ሲሆን የገንዘቡ መጠን ከመግቢያ ትኬት፡ከቶምቦላ እና ሌሎች የገቢ ማስገኛ ዝግጅቶች ላይ የተገኘውን አይጨምርም።
በታዋቂ ኢትዮጵያዊ አርቲስትና የሰብዓዊ መብት ተሟጋች ታማኝ በየነ በተመራው እና እስከ ምሽቱ አምስት ሰዓት በቆየው ደማቅ ዝግጅት ላይ በስቶክሆልም በሌሎችም የስዊድን ከተሞች የሚኖሩ ቁጥራቸው ከሶስት መቶ በላይ የሚገመት ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያው እንዲሁም ስዊድናውያን የተገኙ ሲሆን የክርስትና የእስልምና የሃይማኖት መሪዎችዝግጅቱን በየተራ በመባረክ ከፍተዋል።
ታማኝ በየነ የኢትዮጵያውያ ሳተላይት መገናኛ ብዙሃን የመላው ድምጻቸው የታፈነ ወገኖቻችን ንብረት መሆኑን በጽሁፍና በምስል በተደገፈ ማስረጃ በማስረገጥ በእለቱ ባቀረበው ንግግር ላይ እያንዳንዱ በሃገር ውስጥም ሆነ በውጭ የሚኖር ኢትዮጵያዊ ይህንን ነጻና ከማንም ያልወገነ በዘር በሃይማኖት ወይም በፖለቲካ አመለካከት ላይ የማያዳላ የሚዲያ ተቋም በገንዘብ፡በቁሳቁስ፡እንዲሁም በሌሎች መልኮች ማገዝ የውዴታ ግዴታ እንዳለበት በመጥቀስ ኢሳት እራሱን ችሎ በመቆም ከሶስት ዓመታት በፊት በጥቂት አገር ወዳድ ወገኖች የጀመረውንና ከሰማንያ ሚሊዮን በላይ ዜጎች ነጻና ያልተዛባ ዘገባ እንዲያገኙ የሚያደርገውን ጥረት ከግብ ለማድረስ ሁላችንም የድርሻችንን ማበርከት እንደሚገባን አሳስቧል።
በዝግጅቱ ላይ የ2012 የሂውማን ራይትስ ዋች ድርጅት ተሸላሚና በጸረ ሽብር ወንጀል ተከሶ ስምንት አመት የተፈረደበት የአዲስነገር ኦንላይን አዘጋጅ መስፍን ነጋሽ በበኩሉ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ትናንት በጋዜጠኞች፡በተቃዋሚ ድርጅት መሪዎች እንዲሁም በሌሎች ወገኖች ላይ ሲያደርስ የነበረውን ኢሰብዓዊ እስራት፡ግድያ፡ማዋከብ አጠናክሮ በመቀጠል ዛሬ ደግሞ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያነሱትን የእምነት ነጻነት የማስከበር ጥያቄ ለማፈን የሚያደርገውን ቅጥ ያጣና ሃላፊነት የጎደለው ከአንድ መንግስት የማይጠበቅ ህገወጥ ተግባር በመኮነን እንዲህ አይነቱን የአምባ ገነኖች ወንጀል ለማጋለጥ ኢሳትን የመሰሉ ነጻ የመገናኛ ተቋማትን በተለያዩ መንገዶች መደገፍ ወቅቱ የሚጠይቀን የዜግነት ግዴታ እንደሆነ አስረድቷል።
ሌላው ኢትዮጵያዊ ጋዜጠኛና በስዊድን አገር በሚገኘውና የኢትዮጵያ ድምጽ ሬድዮ ላለፉት አስርት አመታት በማገልገል የሚገኘው አህመድ አሊ በበኩሉ በስልጣን ላይ ያለው የህዋሃት መንግስት የሽብርና የአፈና ተግባር የእያንዳንዱን ኢትዮጵያዊ በር እያንኳኳ መሆኑን በመግለጽ፤ ኢሳትን የመሳሰሉ ድርጅቶችን የዘር፡ሃይማኖት፡ጾታና የፖለቲካ አመለካከቶች ወደ ጎን በመተው በአገር ውስጥም ሆነ በውጭ የምንገኝ ኢትዮጵያውያን አንድ በመሆን ኢሳት የጀመረውን ውጥን ከግብ ለማድረስ እንደሚጠበቅብን አሳስቧል።
በዝግጅቱ ላይ ከ14 ወራት በላይ በቃሊቲ እስርቤት ባልሰራው ወንጀል ሲማቅቅ ቆይቶ ባለፈው መስከረም የተለቀቀው ስዊድናዊ ጋዜጠኛ ማርቲ ሽብዬ በክብር እንግድነት በዝግጅቱ ላይ የተገኘ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት እሱና አብሮት ታስሮ የነበረው ጋዜጠኛው ዩዋን ፐርሹን በኢትዮጵያ ውስጥ ያሳለፉትን የመከራ ጊዚያት የሚተርክ መጽሃፍ ለማሳተም ቀንና ለሊት በመሮጥ ላይ መሆናቸውን በመግለጽ ይህ መጽሃፋቸው ለህትመት እስከሚበቃ ድረስ ግን ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ጊዚያዊ የተኩስ አቁም ማድረጋቸውን በቀልድ መልክ ለኢሳት ቴሌቪዥን ገልጿል። (ዘገባው የቴዎድሮስ አረጋ ነውመሳሳይ )ዘዘ ዘገባቀው ኢሣት የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ላይ የስዊድሽ ፓርላማ አባል ንግግር ያደረጉ ሲሆን የተለያዩ ኢትዮጵያን ብሄሮችን የሚወክሉ ባህላዊ ዜማዎችና ውዝዋዜዎች የዝግጅቱን ታዳሚዎቹረጉ በስዊድን የኢሳት ገቢ ማሰባቢያ ኮሚቴ ለታማኝ በየነና ቤተሰቡ ሜዳሊያና ሽልማት እንዲሁም ዝግጅቱ እንዲሳካ የበኩላቸውን ጥረት ላደረጉ ግለሰቦች የሜዳሊያ ስጦታ በማበርከት ተጠናቋል። ታማኝ በየነ በስዊድን የነበረውን ቆይታ አጠናቆ በዛሬው እለት ኖርዌይ ዋና ከተማ ኦስሎ ላይበሚደረገው ሳሳይ የገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጅት ይገኛል።በበበበበ
ለኢሳት ቴዎድሮስአረጋ
በተመሳሳይ ዜናም በኖርዎይ የሚገኙ ኢትዮጵያዊያን በጉጉት ሲጠባበቁት የነበረው የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራም እጂግ በተሳካ ሁኔታ የተጠናቀቀ ሲሆን በዚሁ ዝግጂት ከ 500 በላይ ኢትዮጵያዊያን የዝግጂት አዳራሹን አጨናንቀውት፣ ለእለቱ ፕሮግራም ደግሞ ድምቀት ሰጥተውት አምሽተዋል። በዚሁ ምሽት የቀድሞው የኮከብ አርቲስትነት ብቃትና ችሎታው አሁንም ያልተለየው አክቲቪስት ታማኝ በየነ በተያዘለት ፕሮግራምና ሰአት በዝግጂቱ አዳራሽ በመገኘት እለቱን እጂግ አስደሳችና የማይረሳ ምሽትም አድርጎታል፣ ፣
የገቢ ማሰባሰቢያ ፕሮግራሙ የተጀመረው፣ አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ገና ወደ አዳራሹ ከመድረሱ ሰአታት በፊትና አዳራሹ በኢትዮጵያ አረንጓዲ ቢጫ ቀይ ባንዲራ አምሮና ደምቆ በታዳሚዎች ተሞልቶ ነበር። እንደ ኖርዎይ ሰአት አቆጣጠር 16:30 ላይ አክቲቪስት ታማኝ ወደ አዳራሹ ሲገባ የኢትዮጵያን ባንዲራ በነፍስ ወከፍ የያዙት ኢትዮጵያዊያን ባንዲራቸውን በማውለብለብ በከፍተኛ ስሜትና ድምቀት ተቀብለውታል፣ ፣
በዚሁ እለት ዝግጂት ለታማኝ የእንኳን ደህና መጣህ ንግግር ከዝግጂቱ አስተባባሪ ተወካይ አቶ ማተቤ መለሰ የተደረገ ሲሆን፣ ከዚሁ በማስከተል የኢትዮጵያ ማህበር በኖርዎይ ተወካይ፣ የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ማህበር በኖርዎይ ተወካይ፣ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር በኖርዎይ ተወካይ፣ እንዲሁም አቶ ዩሱፍ ያሲን በምስራቅ አፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኝ፣ ንግግር አድርገዋል ።
ሁሉም ንግግር አድራጊዎች፣ ኢትዮጵያ ውስጥ መንግስት በኢትዮጵያዊያን ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍና በደል በጽኑ ያወገዙ ሲሆን፣ የኢትዮጵያዊያን ህዝብ አይንና ጆሮ ለሆነው ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ድጋፍ የማድረግ ብቻ ሳይሆን በሃሳብም የማገዝ የዜግነት ግዴታና ሃላፊነት እንዳለበት አስገንዝበዋል። ለአርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ያላቸውን አክብሮት፣ ፍቅርና፣ አድናቆትም ገልጸዋል፣ ፣
የምስራቅ አፍሪቃ ቀንድ የፖለቲካ ተንታኙ አቶ የሱፍ ያሲን፣ ኢሳት አልጀዚራን ሊሆን አይችልም ወይ በሚል ርእስ አጭር ጥናታዊ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን፣ በዚሁ ጽሁፋቸው የኢሳትና አልጃዚራ ቴሌቪዥን ያላቸውን ልዩነትና ተመሳሳይነት ዳሠዋል። በመጨረሻም ኢሳት የኢትዮጵያዊያን አልጃዚራ የማይሆንበት ምንም ምክንያት አለመኖሩንና አሁን ባለው ሂደት ከቀጠለም ይህን እውነታ በአጭር ጊዜ ውስጥ ለማየት እንደምንበቃ እምነታቸውን ገልጸዋል።
የአቀባበል ንግግሮቹ ከተጠናቀቁ በኋላ፣ የእራት ረፍት የተደረገ ሲሆን፣ ከእራት በኋላ የነበረውን ስፊ ጊዜ አርቲስትና አክቲቪስት ታማኝ በየነ ተረክቡዋል። ታማኝ በየነ፣ እስካሁን ድረስ ባልተለየው የአርቲስትነት ብቃቱ የዝግጂቱን ተሳታፊዎች እያዝናና የገቢ ማሰባሰብ ዝግጂቱን አከናውኗል፣ ፣ እግዚአብሄርን በማመስገንና ሙስሊም ወንድሞቻችንንም አሰላም አለይኩም በማለት ንግግሩን የጀመረው አርቲስት ታማኝ በተለይም ባሁኑ ወቅት መንግስት በሙስሊም ወገኖቻችን ላይ እያደረሰ ባለው ግፍና በደል ዙሪያ ከበቂ መረጃዎች ጋር በማስደገፍ የተሰብሳቢዎችን ቀልብ ስቦ አምሽቷል።
በዚሁ የኖርዎይ ኢሳት ገቢ ማሰባሰቢያ ዝግጂት ከጫረታ ብቻ ከ160 ሺህ የኖርዌጂያን ክሮነር በላይ የተገኘ ሲሆን በእለቱ ከነበሩት ሌሎች የገቢ ማስገኛ ዝግጂቶች ማለትም ከመግቢያ ትኬት ሽያጭ፣ ከሎተሪ ሽያጭ፣ ከምግብና መጠጦች ሽያጭ፣ ከቲሸርቶች፣ ኮፍያ፣ ባንዲራና ሌሎችም ቁሳቁሶች ሽያጭና ሌሎችም በርካታ ገንዘብ እንደሚገኝ ይጠበቃል፣ ፣
ዝግጂቱ መጠናቀቂያ አካባቢ ላይ የኢትዮጵያ ስደተኞች ማህበር አባላት ድራማና ስነ ጽሁፍ ያቀረቡ ሲሆን አርቲስት ታማኝ በየነ ደግሞ ከዴሞክራሲያዊ ለውጥ በኢትዮጵያ ድርጂት በኖርዎይ የተዘጋጀለትን የአጼ ምንሊክ ፎቶግራፍ ከሊቀመንበሩ አቶ ዳዊት መኮነን እጂ ተቀብሏል፣ ፣ አቶ ዳዊት ስጦታውን ለአክቲቪስት ታማኝ ሲያበረክቱ አንተ የዘመናችን ምኒሊክ ነህ እናም ይህ ምስል ብቻ ሳይሆን መልእክቱም ላንተ ይገባሃል ብለዋል። አቶ ዳዊት ኢሳትን አስመልክቶ ደግሞ ናይጀሪያዊያን አንድ አባባል አላቸው- ትልቁ ዶሮ እንቁላል ነበር የሚል- እናም በሁለት እግሩ እየቆመ ያለው የዛሬው ኢሳት ነገ የምንፈልገው ደረጃ ላይ ደርሶ እንደምንመለከተው ርግጠኛ ነኝ ብለዋል።
በእለቱ ዝግጂት ኢትዮጵያዊያን ሙዚቀኞች እንግዶችን በሙዚቃ ሲያዝናኑ ያመሹ ሲሆን፣ ፕሮግራሙ ሲጠናቀቅ የምስጋናና የመሰነባበቻ ንግግር በዶር ሙሉ አለም አዳም አቅርበዋል።