አቶ በረከት ስምኦን ተቃውሞ ገጠማቸው

(ኢሳት ዲሲ–ነሐሴ 23/2010) አቶ በረከት ስምኦን በተለያዩ መገናኛ ብዙሃን እየሰጧቸው ያሉ አስተያየቶች በማህበራዊ ድረገጾችና በበርካታ ኢትዮጵያዊያን ተቃውሞ  ገጠመው።

አስተያየት ሰጭዎች እንደሚሉት አቶ በረከት ሕዝቡን ከለውጥ አራማጆች ጋር በማጋጨት የመከፋፈል ስራ እየሰሩ ነው።

በቅርቡ ከብአዴን ማእከላዊ ኮሚቴ አባልነት የታገዱት አቶ በረከት ስምኦን የኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮችንና የለውጥ አራማጆችን ማውገዛቸው በሕዝቡ ዘንድ ቁጣን ፈጥሯል።

አቶ በረከት በተለይም ከብአዴን አመራር አባላት መካከል ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮንን እና አቶ ገዱ አንዳርጋቸውን የመምራት ብቃት የላቸውም ማለታቸው ይታወሳል።

የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሃይለማርያም ደሳለኝን ደግሞ ህገመንግስቱን ያላነበቡና መወሰን የማይችሉ ሲሉ አጣጥለዋቸዋል።