ሰኔ አስራ ሦስት ቀን ፳፻፬ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-የገንዘብ ልማት ሚኒስቴር ዲኤታ የሆኑት አቶ አህመድ ሼዲ እና የአሜሪካ አለማቀፍ የልማት ድርጅት ዳይሬክተር የሆኑት ሚ/ር ቶማስ ስታል ስምምነቱን ፈርመዋል።
ገንዘቡ ለትምህርት ለጤናና ለመልካም አስተዳዳር ግንባታ እንደሚውል የልማት ድርጅቱ ዳይሬክተር ተናግረዋል።
አሜሪካ ይህን ያክል ገንዘብ ለኢትዮጵያ ስትለግስ የአሁኑ የመጀመሪያ ነው።
ኢትዮጵያ በሰብአዊ መብት አያያዙዋ በስቴት ዲፓርትመንት ሳይቀር ክፉኛ ብትተችም፣ አሜሪካ መንግስት አሁንም ለኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ የሆነ እገዛ እያደረገ ነው።
ምሁራን እንደሚሉት የገንዘብ እርዳታው ኢትዮጵያ በሶማሊያና በሱዳን ሰራዊቷን በመላክና ሽብረተኝነትን በመዋጋቷ እንዲሁም በአርባ ምንጭ አካባቢ የሚገኘውን አየር ማረፊያ ለአሜሪካ ሰው አልባ ቃኝ ጀቶች ማረፊያ በመለገሷ የተሰጠ “የእናመሰግናለን” ስጦታ ነው።
የመለስ መንግስት የአሜሪካ ጉዳይ አስፈጻሚ ነው እየተባለ ይተቻል።
ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.
ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide