አሜሪካዊ የአኟዋክ ተወላጆች በቦሌ ለ 48 ሰአት ታሰሩ

ህዳር ፲፯ (አስራ  ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የኢትዮጵያ መንግስት ሁለት ኢትዮጵያዊ የአሜሪክላ ዜጎችን ለ 48 ሰአታት ማሰሩ ተሰማ። በኢትዮጵያ የአሜሪካ ኤምባሲ ከመንግስት ሰዎች ጋር ተሞግቶ እንዳስፈታቸውና ከቦሌ በቀጥታ ወደ አሜሪካ እንደላካቸው ተገልጾል።

የአኟዋክ ብሄር ተወላጅ የሆኑትን አሜርካዊያንን ከቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይዞ ያሰረው የኢትዮጵያ መንግስት ግለሰቦቹ መንግስታዊ ያልሆነ ድርጅት ልመመስረት ወደ ጋምቤላ መጓዛቸውን ቢገልጹም የለም የፖለቲካ አጀንዳ አላችሁ፤ ታጣቂዎችን ትደግፋላችሁ በማለት መሆኑን የኢሳት ምንጮች ገልጸዋል።

ለድርጅት ምስረታ ወደ ኢትዮጵያ ተጉዘው የነበሩት ሁለቱ የአኙዋክ ተወላጆች አሜሪካዊያን ለዚህ ፕሮጀክት ወደ ጋምቤላ በተጓዙበት ጊዜ ስራቸው ል፤አይ የክልሉ ሀላፊዎች ችግር በመፍጠራቸው ረሰ መስተዳድሩ ጋር ቀርበው በክልሉ ስላለው የአሰራር ብሉሹነትና ሙስና መናገራቸውን ለማወቅ ተችሎል።

ምንጮቻችን እንደገለጹት ምናልባትም በቦሌ እንዲያዙ ምክንያት የሆነው የክልሉ መስተዳድር ለፌደራል ባለስልጣናት ግለሰቦቹ አስተዳደራቸውን መተቸታቸውን በመናገራቸው ሊሆን ይችላል ብለዋል።

አሜሪካዊ ዜግነት ያላቸው ሁለቱ የአኝዋክ ተወላጆች ል 48 ሰአታት ከታሰሩ በሆላ የአሜሪካ ኤምባሲ ዜጎቼ ይፈቱ ብሎ በመጠየቁ መፈታታቸውንና ከዛው ከአውሮፕላን ማረፊያ ወደ አሜሪካ መላካቸውን ለማወቅ ተችሎል።