በመቀሌ ዩኒቨርሲቲ ሙስና ተስፋፍቷል

ህዳር ፲፯ (አስራ  ሰባት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-በጀርመናዊ ፕሬዚዳንት የሚመራው የመቀሌ ዩኒቨርሲቲ በሁለት ምክትል ፕሬዚዳንቶች ብቻ ከ 300 ሚሊዮን ብር በላይ መባከኑ ተገለጠ።

ሁለቱን ምክትል ፕሬዚዳንቶች ይነሱልኝ ሲሉ ለትምህርት ሚስቴር ሳይቀር ደብዳቤ የጻፉት ጀርመናዊ ፕሬዚዳንት ማስፈራሪያና ዛቻ ደርሶባቸዋል ተብሎል።

ከኢትዮ ሚዲያ ያገኘነው መረጃ እንዳመለከተው በ300 ሚሊዮን ብር ሙስና የተጠረጠሩትን የዩኒቨርሲቲው ምክትል ፕሬዚዳንቶች ዶ/ር ክንድያ ገ/ህይወትና ዶ/ር አብድርቃድር ከድር ናችው።

አቶ መለስ በህይወት በነበሩ ጊዜ ግንኙነታቸው ቀጥታ ከሳቸው ጋር ነበር የሚባሉት ጀርመናዊ ፕሬዚዳንት በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ ገንዘብ እየባከነ መሆኑን ገልጸው ለሚመለከተው የመንግስት አካል ደብዳቤ በመጻፋቸውና ለት/ሚኒስቴርም ግልባች በመላካቸው በቦርድ ሰብሳቢው በአቶ ቲዎድሮስ ሀጎስ ሳይቀር ማስፈራራት እንደተደረገባቸው ኢትዮ ሚዲያ ዘግቦል።