በጎንደር ከቤት ማፍረስ ጋር በተያያዘ በተነሳ ረብሻ 3 ሰዎች ተገደሉ

ሚያዚያ ፳፫ (ሃያ ሦስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ዛሬ ጧት ገንፎ ቁጭ በሚባለው አካባቢ በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ ቀለም የመቀባት ስራ በተጀመረበት ወቅት ረብሻ መቀስቀሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የፌደራል ፖሊስ በወሰደው የሃይል እርምጃ አንድ ሰው ሲገደል የአካባቢው ነዋሪ በወሰደው የአጸፋ እርምጃ ደግሞ አንድ ፖሊስና አንድ ታጣቂ ሚሊሺያ ተገድለዋል።

የፌደራል ፖሊሶች በርካታ ወጣቶችን ይዘው ያሰሩ ሲሆን፣ አንዳንዶች አካባቢውን ጥለው መሸሻቸው ታውቋል።