በየወሩ 45 ሺህ ሴቶች ወደ ሳዓዲ ዐረቢያ ሊላኩ ነው

መጋቢት 8 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ኢትዮጵያ በየወሩ 45 ሺህ  ሴቶችን ወደ ሳዓዲ ዐረቢያ ለመላክ መዘጋጀቷን ሳዓዲ ጋዜጣ  ዘገበ።

ጋዜጣው በሳዑዲት ዐረብ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ምንጮቹን ጠቅሶ ከጂዳ እንደዘገበው፤ 45 ሺህ ኢትዮጵያውያን ሴቶች በየወሩ ወደ ሳዑዲ የሚመጡት በቤት ሠራተኝነት ለማገልገል ነው።

 የሳዑዲ መንግስት ኬንያን ጨምሮ ከአራት አገሮች ለቤት ሠራተኝነት ወደዚያው የሚያቀኑ ሴቶችን በህግ እንዳይገቡ ካገደ በሁዋላ ኢትዮጵያውያን የቤት ሠራተኞች ተፈላጊነታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን “አሻርክ አል-አውሳት” የተሰኘው ሌላው  የአገሪቱ ጋዜጣ  ዘግቧል።

ከሌሎች አገሮች የሚደረገው ጉዞ የተቋረጠው፤የ ሳዑዲ መንግስት ከየ አገሮቹ ጋር በገባው ስምምነት መሰረት ለሴቶቹ ለማሟላት የገባውን ቃል ሊጠብቅ ባለመቻሉ እንደሆነ ተመልክቷል።

ባለፈው ታህሳስ ወር ማብቂያ ሪያድ ውስጥ የገናን በዓል ለማክበር በአንድ ቤት ውስጥ ለጸሎት በመሰብሰባቸው ምክንያት ለአስከፊ እስራትና እንግልት ከተዳረጉት 30 ኢትዮጵያውያን መካከል፤ አብዛኞቹ ሴቶች እንደሆኑ መዘገቡ ይታወሳል።

በጂዳ የ ኢኮኖሚ ጉዳዮች ምክትል ካውንስል ኑር አደን ማስፋ፤የ እርሳቸው ዲፓርትመንት ከ ኢትዮጵያ ሠራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር ከተውጣጣ ኮሚቴ ጋር ለበርካታ ጊዜያት በመገናኘት  ሶቶች ሥልጠና ከወሰዱ በሁዋላ ወደ ሳዑዲ አረቢያ ሄደው የሚሠሩበትን ሁኔታ ማመቻቸታቸውን ተናግረዋል።

በሊባኖሳዊ አሠሪዎቿ በጎዳና ላይ እየተጎተተች ስትንገላታና  ድረሱልኝ እያለች ስትማፀን የታየችው ኢትዮጵያዊቷ ዓለም ደቻሳ ሆስፒታል ከገባች በሁዋላ ራሷን በፎጣ አንቃ ያጠፋችው ከቀናት በፊት ነበር።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide