በኮምቦልቻ የባቡር ሃዲድ ሰራተኞች የስራ ማቆም አድማ አደረጉ
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 02 ቀን 2010 ዓ/ም ) ያፒ መርከዚ በተባለ የቱርክ ኩባንያ ከ አዋሽ ኮምቦልቻ ወልድያ ሀራ ገበያ በሚሰራው የባቡር መንገድ ዝርጋታ ስራ ላይ የሚሰሩ ሰራተኞች ትናንት ወደ አደባባይ በመውጣት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገው የነበረ ቢሆንም፣ ከደቡብ ወሎ ባለስልጣናት ጋር ባደረጉት ውይይት ከኩባንያው መሪዎች ጋር ለመነጋጋር ቀጠሮ የያዙ ሲሆን፣ ማኔጅመንቱ ለጥያቄያቸው መልስ እስከሚሰጥ አድማ በማድረግ ላይ መሆናቸውን ሰራተኞች ገልጸዋል።
የዞኑ አመራሮች ሰራተኞች ስራ እንዲጀምሩ ቢጠይቁም፣ ሰራተኞች መልስ ካልተሰጠን ስራ አንጀምርም በማለት በአድማው ገፍተውበታል።