ሰኔ ፮(ስድስት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-አክራሪ የሚባሉት ታጣቂዎች በአጭር ጊዜ ውስጥ የኢራቅን ሁለተኛ ከተማ መቆጣጠራቸውን አለማቀፍ መገናኛ ብዙሀን ዘግበዋል።
ታጣቂዎቹ ባግዳድን ለመያዝ እንቅስቃሴ ለመጀመር በሚሞክሩበት ሰአት አሜሪካ መንግስት ለኑር አልማለቂ መንግስት ወታደራዊ ድጋፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል። የሺአ እምነት ተከታዮች የሚበዙባት ኢራን ለአልማላቂ መንግስት ድጋፍ ለማድረግ ጦሩዋን ማስገባቱዋትም ተውቋል።
በኢራቅ የሺአ የሃይማኖት መሪ የሆኑት አያቶላ አል ሲስታኒ የሺአ እምነት ተከታዮች መሳሪያ አንስተው እንዲዋጉ ጥሪ አቅርበዋል። የኑር አልማላቂ መንግስት ሺ አዎችን በመንግስታዊ ቦታዎች ላይ በመሾም ሱኒዎችንና ኩርዶችን ማስከፋቱን ዘገባዎች ያመለክታሉ።