በአዲስ አበባ ከ20 በላይ ነጋዴዎች ታሰሩ

ግንቦት ፳፩(ሃያ አንድ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፌደራል ፖሊስ ራጉኤል አካባቢ የሚገኙ  በኮንትሮባንድ የገቡ የሞባይል ቀፎዎችን ይሸጣሉ ያላቸውን ነጋዴዎች ይዞ አስሯል። በድርጅቶቻቸው ውስጥ ያለውን ንብረት መውሰዱንም ነጋዴዎች ለኢሳት ገልጸዋል።

አብዛኞቹ የሞባይል ቀፎዎች ከቻይና የመጡና በአብዛኛው አዲስ አበባ ክፍል አገልግሎት እየሰጡ እንደሚገኙ የሚገልጹት የታሳሪ ነጋዴ ቤተሰቦች፣ እቃዎቹ ወደ አገር ውስጥ በኮንትሮባንድ ገብተዋል ከተባለም ከዋናው ከምንጩ ማደረቅ እንጅ እነሱ ተረክበው በሚያከፋፍሉት ላይ እርምጃ መወሰዱ እንዳሳዘናቸው ገልጸዋል።

በጉዳዩ ዙሪያ የአዲስ አበባን ፖሊስ ለማነጋገር ያደረግነው ሙከራ አልተሳካም።