ሰኔ ፲፪ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:- የአዲሱ ገበያና የቀጨኔ አካባቢ ነዋሪዎች የውሃ እጥረቱ ለኢኮኖሚና ለጤና ቀውስ እንደዳረጋቸው ተናግረዋል።
በዚህ ዓመት በተደጋጋሚ ከአንድ ወር በላይ የቆየ የውሃ እጥረት እንዳጋጠማቸው ነዋሪዎቹ ገልጸዋል።
መንግስት ” የአራዳና ጉለሌ ክፍለ ከተሞች የቦታ አቀማመጥ ለውሃ ሥርጭቱ አመቺ አለመሆን፣ በእነዚህ ክፍለ ከተሞች ከፍተኛ የሕዝብ ቁጥር መጨመር ፣ በተለያዩ የልማት ሥራዎች ምክንያት የውሃ መስመሮች መሰበርና መቆረጥ እንዲሁም በውሃ ማጠራቀሚያ ታንከሮች አካባቢ ተደጋጋሚ የመብራት ኃይል መቋረጥ” ለውሃ እጥረት መፈጠር ምክንያቶች መሆናቸውን ገልጿል።
ነዋሪዎቹ ችግሩን በጊዜያዊነት ለመፍታት ውሃን በፈረቃ የሚያገኙበት መንገድ መመቻቸቱን አንድ የመንግስት ባለስልጣን ተናግረዋል።፡