ኢሳት ዜና:- በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በእስር ላይ የሚገኙ ጋዜጠኞችና የፖለቲካ ድርጅት መሪዎች እንዲፈቱ ለመጠየቅ በኋይት ሀውስ ፊት ለፊት የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዐት ሊያደርጉ ነው::
ማርች ፎር ፍሪደም ለኢሳት በላከው መግለጫ ላይ እንዳመለከተው ኢትዮጵያኑ ኖቪምበር 6 በኋይት ሀውስ ለፊት ከ6ፒኤም ጀምሮ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዐት በማድረግ በእስር ላይ የሚገኙት ጋዜጠኞችና ፖለቲከኞች እንዲፈቱና የኦባማ አስተዳዳር በመለስ ዜናዊ አገዛዝ ላይ ጫና እንዲያሳርፉ ይጥይቃሉ።
በስነስርአቱ ላይ ወ/ት ብርቱካን ሚዴቅሳ እንደሚገኙም ማርች ፎር ፍሪደም አስታውቋል።በቅርቡ ተመሳሳይ የሻማ ማብራት ሥነ-ሥርዐት በዚሁ በኋይት ሀውስ ፊት ለፊት መካሄዱ ይታወሳል።