በአማሮ ወረዳ የኦነግ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎች ገደሉ

(ኢሳት ዲሲ–ጥር 20/2011)በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በአማሮ ወረዳ የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ኦነግ ታጣቂዎች ሁለት ሰዎች መግደላቸውን የወረዳው ባለስልጣን ለኢሳት ገለጹ።

ፋይል

የወረዳው የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ አገኘሁ በቀለ ለኢሳት እንደገለጹት በትላንትናው ዕለት ሻሮ በተሰኘ ቀበሌ የገቡት የኦነግ ታጣቂዎች ሁለት ሰው ገድለው ከብቶችን ዘርፈው ወጥተዋል።

ኦነግ ከመንግስት ጋር ለሁለተኛ ጊዜ ስምምነት ማድረጉና ዕርቅ መፈጸሙ እየተገለጸ ባለበት ሁኔታ የአማሮው ጥቃት መካሄዱ ስጋትን ፈጥሯል።

በጉዳዩ ላይ የኦነግን ምላሽ ለማግኘት ያደረግነው ጥረት አልተሳካም።