በትግራይ ክልል የፌደራል ፖሊስ አባላት በቁጥጥር ስር ዋሉ መባሉ ትከክል አይደለም ሲል ፖሊስ አስታወቀ

(ኢሳት ሐምሌ 27/2010) የፌደራል ፖሊስ ኮሚሽን ባወጣው መግለጫ የ መከላከል አባላት ዋሉ ተብሎ እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክል አይደለም ብሎአል። በወንጀል መከላከል ዘርፍ የፀረ-ሽብርና የተደራጁ ወንጀሎኞች ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር ረ/ኮሚሽነር አበራ ሁንዴ እንደገለፁት፣ የሃገሪቱ ክልሎች የፖሊስ አባላትን እንደሚያሰማሩ ተናግረው፣ በትግራይ ክልልም አባላቱን በማሰማራት ከክልል ፀጥታ አካላት ጋር በመሆን እየሰሩ እንደሚገኙ ገልፀዋል፡፡ “በማህበራዊ ሚዲያ የፖሊስ አባላቱ መቀሌ አየር ማረፊያ ላይ በክልል የፖሊስ ኃይሎች ተይዘዋል ተብሎ የተሰራጨው መረጃ ከእውነት የራቀና አሉባልታ” እንደሆነ ባለስልጣኑ ተናግረዋል።
የቢቢሲ አማርኛው ክፍልና የጀርመን ድምጽ አማርኛው ክፍል ከ40 ያላነሱ የፌደራል ፖሊስ አባላት መቀሌ አየር ማረፊያ ላይ በትግራይ ክልል ፖሊሶች መታገታቸውን ዘግበው ነበር።