በቤንች ማጂ ዞን በማጂ ወረዳ ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሆስፒታል ስራ ባለመጀመሩ ህዝቡ ምሬቱን እየገለጸ ነው
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 22 ቀን 2010 ዓ/ም ) የአካባቢው ነዋሪዎች እንደሚሉት የዞኑ ዲዛይን እና ኮንስትራክሽን መምሪያ እና ግንባታውን ያከናወነው ድርጅት ርክክብ ባለመፈፀማቸው ሆስፒታሉ አገልግሎት መስጠት አልቻለም። የጤና ባለሙያዎች የተመደቡ ቢሆንም፣ አገልግሎት መስጠት አልቻሉም። ለተከታታይ ህክምና ታማሚዎች ህክምና እየተሰጠ ያለው ከ 40 አመት በላይ እድሜ ባለው የማጂ ጤና ጣቢያ ሲገነባ ለባለሙያዎች ማረፈያነት በተሠራዉ በጣም ጠባብ እና የሚያፈስ ክፍል ውስጥ በሸተኞችን በማጎር በመሆኑ ለተጨማሪ በሽታዎች እየተጋለጡ ነው። ነፍሰጡር እናቶች በየመንገዱ በጉዞ ላይ ህይወታቸው እያለፈ በመሆኑ የአካባቢው ባለስልጣናት ፈጣን ውሳኔ እንዲሰጡበት ነዋሪዎች ጠይቀዋል።