በቀጣዩ የህወኃት ጉባኤ፣ ለውጡን የማይደግፈው ቡድን ስልጣን ላይ ከወጣ በሀገሪቱ ሰላም አይኖርም” ሲሉ ጀነራል ጻድቃን ገብረተንሳይ አስጠነቀቁ ።
( ኢሳት ዜና ነሐሴ 14 ቀን 2010 ዓ/ም ) የቀድሞው ኢታማዦር ሹም በወቅቱ ሀገራዊ ጉዳይ ዙሪያ ከአዲስ አድማስ ጋር ባደረጉት ቃለ ምልልስ፣በክልሉ በትግራይ ወጣቶችና ምሁራን ዘንድ ከመቼውም ጊዜ በላይ የለውጥ ጥያቄዎች እየተሰሙ መምጣታቸውን በመጠቆም፣ ይሑንና ሕዝቡ የለውጡ አጋር እንዳይሆን በህወኃት አመራሮች ተጠፍንጎ መያዙን አስረድተዋል።
“ህወሓት ዋነኛውን ስልጣን ይዞ በነበረበት ወቅት ሰብአዊ መብትና ዲሞክራሲያዊ መብትቶችን ረግጦ ነው ሲገዛ የቆየው” ያሉት ጀነራል ጻድቃን፤”ህወኃትንለ40 ዓመት ሲመሩት የነበሩ ሰዎች አሁን ህዝቡ እንደማይፈልጋቸው ያውቃሉ”ብለዋል።
ሕወሓትና የትግራይ ሕዝብ አንድ ነው ማለት የትግራይን ሕዝብ ማሳነስ እንደሆነ የገለጹት ጀነራል ጻድቃን፣ የህወሃት ጉባኤ ዋና አጀንዳ መሆን ያለበት የፖለቲካ ሪፎርም አጀንዳ ነው ሲሉ አሣስበዋል።
“በለውጡ ጥቅማቸው የተነካባቸው እነዚሁ የሕወሓት አመራሮች በሕዝቡ ላይ ቤንዚን እያርከፈከፉ ነው” ያሉት ጀነራሉ፣”የትግራይን ሕዝብ እንደምርኮ መያዣ ያደረገው ኃይል ከጨዋታው ካልወጣ ፣ለትግራይ ብቻ ሳይሆን ለሀገርም አደጋ ይሆናል “ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
የቀድሞው አየር ኃይል አዛዥ ሜልጄር ጀነራል አበበ ተክለሃይማኖት በበኩላቸው ከጥቂት ጊዜ በፊት በጉዳዩ ዙሪያ ባደረጉት ንግግር መቀሌ የመሸጉትን የህወሃት አመራሮች ያሣሰባቸው የትግራይ ሕዝብ ጉዳይ ሳይሆን የራሳቸው ስልጣንና ጥቅም ማጣት እንደሆነ በማብራራት፤ ሕዝቡ የለውጡ አጋር በመሆን ፋንታ በጡረታ የተሰናበቱ የህወኃት ሰዎችን ተከትሎ ወደ ገደል እንዳይገባ ማስጠንቀቃቸው ይታወሳል። ይህ በእንዲህ እንዳለ የቀድሞው የመንግስት ቃል አቀባይና በአሁኑ ወቅት ከለውጡ ተቃዋሚዎች መካከል የሚጠቀሱት የህወኃቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ አባል አቶ ጌታቸው ረዳ የኢትዮጵያን ሕዝብ ፡ማዬት የማይችል” ሲሉ በጅምላ ዘልፈዋል።
አቶ ጌታቸው ረዳ ቀደም ሲልየመንግስት ቃል አቀባይ በነበሩበት ወቅት በህዝባዊ አመጹ በመበሳጬት አንድን ሕዝብ “አጋንንት”ብለው መዝለፋቸው ከፍ ያለ ተቃውሞ እንዳስነሳባቸውና በተቃውሞው በመደንገጥ አባባሉን ለማስተባበል መሞከራቸው ይታወሳል።
ከዚያም በማስከተል የሕወሓትን የልዩነት ሤራ በማክሸፍ በኦሮሞና በአማራ ተወላጆች መካከል እየተጠናከረ በመጣው ሕብረት በመበሳጬት “ ሁለቱ እሳትና ጭድ የሆኑ ኃይሎች በአንድ ላይ መነሳታቸው ፣የነሱን ጥንካሬ ሳይሆን የኛን ምንም አለመሥራት፣የኛን ድክመት ነው የሚያሳዬው”በማለት በአደባባይ መናገራቸው አይዘነጋም።
በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ እያስተናገደችው ያለው ለውጥ ያልተዋጠላቸው አቶ ጌታቸው ረዳ ሰሞኑን ደግሞ ፦”በማለት ለውጡን በበጎ መልክ የተቀበለውን ሕዝብ በጅምላ “ማዬት የማይችል” በማለት ዘልፈዋል።