በሺኒሌ ዞን ያለውን ተቃውሞ ተከትሎ ዜጎች በገፍ እየታሰሩ ነው
(ኢሳት ዜና ሚያዝያ 17 ቀን 2010 ዓ/ም) በረባራት እየተባሉ የሚጠሩ ወጣቶች በአቶ አብዲ ኢሌ አገዛዝ በመማረር የጀመሩትን ተቃውሞ ተከትሎ በርካታ ወጣቶች ተይዘው ታስረዋል።
በርካታ ወጣቶች በተለያዩ እስር ቤቶች ውስጥ እንደሚገኙ የገለጹት ምንጮች፣ የእስር ዘመቻው ተጠናክሮ በመቀጠሉ አካባቢው በውጥረት እንደሚሞላ አድርጎታል።
ከፍተኛ ቁጥር ያለው ሰራዊት በአካባባቢው በማሰማራት ተቃውሞውን ለማፈን ጥረት መደረጉን የአካባቢው ነዋሪዎች ይናገራሉ።
ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የኢትዮ-ሶማሊው ክልል መሪ አቶ አብዲ ኤሌ የሚፈጽሙትን ከፍተኛ የሰብአዊ መብት ጥሰቶች የሚያወግዙ የውስጥና የውጭ ተቃውሞዎች እየበረከቱ ነው።
የአሜሪካ መንግስት ባወጣው አመታዊ የስብአዊ መብት ሪፖርት በሶማሊ ክልል በ2009 ዓም ከ100 በላይ ሰዎች መገደላቸውን ገለጾ ነበር። ግድያውን የሚፈጽሙት ደግሞ የሶማሊ ልዩ ሃይል አባላት ናቸው።