በሰሜን ጎንደር ፍጥጫው ከፍተኛ ደረጃ ላይ ደርሷል

ግንቦት ፳፰ (ሃያ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ከዋልድባ ገዳም ጋር በተያያዘ በሰሜን ጎንደር ህዝብና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ፣ ሊፈነዳ መቃረቡን ዘጋቢዎች ከስፍራው ገልጠዋል።

የአካባቢው ህዝብ ስንቁን እየያዘ ወደጋዳሙ በመትመም ላይ ሲሆን፣ መንግስትም በደባርቅና አካባቢው በብዙ መቶዎች የሚቆጠሩ የፌደራል ሰራዊቱን በትኖአል።

አንድ ስማቸው እንዳይገለጥ የፈለጉ ሰው፣ በህዝቡና በመንግስት መካከል ያለው ፍጥጫ በመጨመሩ ምናልባትም ሰኔ 21 ግጭት ሊፈጠር ይችላል ሲሉ ስጋታቸውን ገልጠዋል። የአገር ሽማግሌዎች፣ ቀሳውስቱና ታዋቂ ሰዎች ችግሩን ለመፍታት በዛሬማ ወንዝ አካባቢ ውይይት እያደረጉ ቢሆንም፣ እስካሁን ድረስ መፍትሄ ላይ ሊደርሱ አልቻሉም። የአካባቢው ሰዎች እንደሚሉት ከሆነ ግን ችግሩ በውይይት የሚፈታ አይሆንም። መንግስት ድርጊቱን እስካላቆመ ደረስ ተቃውሞው ይቀጥላል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ 5 ካህናት በደባርቅ መታሰራቸው ታውቋል።

በቅርቡ ስለሺ ጥጋቤነህ የተባለ የደባርቅ ነዋሪ መታሰሩ ይታወሳል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide