የካቲት ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-ቢቢሲ እንደዘገበው ጅራታም ኮከብ ወይም ሜትዮሩ የወደቀው በሩሲያ የኡራል ተራራ ላይ ሲሆን፣ 950 የሚሆኑ ሰዎች ተጎድተዋል።
አብዛኞቹ በተለያዩ መጠኖች ቁስለት የደረሰባቸው ሲሆን፣ 46 ሰዎች ሆስፒታል ገብተዋል።
ፕሬዚዳንት ፑቲን ሜትዮሩ በመኖሪያ ሰፈር ላይ ባለመውደቁ እግዚአብሄርን አመስገንዋል።
ሜትዮሩ ከመሬት ጋር በሚላተምበት ጊዜ ከፍተኛ የሆነ ፍንዳታ መሰማቱ ታውቋል። አንዳንድ ፖለቲከኞች በበኩላቸው የወደቀው ሜትዮር ሳይሆን የአሜሪካ አዲስ የጦር መሳሪያ ነው።
የሩስያ ሳይንቲስቶች 10 ሺ ኪሎግራም የሚመዝነው ሜትዮር በሰአት 54 ሺ ኪሎሜትሮችን ይጓዝ ነበር።