ነሃሴ ፳፬(ሃያ አራት)ቀን ፳፻፭ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ኢሳት ከኪራይ ቤቶች ድርጅት ባገኘው መረጃ በአዲስ አበባ የተገነቡ 2345 ቤቶች ለሚኒስትሮች እና ለአዲስ አበባ ከተማ መስተዳድር ባለስልጣናት ተሰጥተዋል።
የቤቶች ልማት ባካሄደው ጥናት ፣ አብዛኞቹ ባለስልጣናት የግል ቤቶቻቻውን በማከራየት በመንግስት ቤቶች ውስጥ ይኖራሉ። ኪራይ ቤቶች ቤቶቹን እንዲለቁ ሲጠይቃቸው በግል የገነቡዋቸው ቤቶች ለደህንነታቸው ዋስትና እንደማይሰጡ በመከራከር ቤቶቹን ለማስረከብ ፈቃደኞች አልሆኑም።
በትግራይ ክልለ በመቀሌ 375 ፣ በውቅሮ 96 ፣ በአዴግራት 67፤ አክሱም 86፣ማይጨው 99 ፤ በኦሮምያ ክልል ናዝሬት/ አዳማ 215፣ ጅማ 93፣ ቢሾፍቱ 102 ፣ አንቦ 68 ፤ወሊሶ 94፤ነቀምት 77 ፤አሰላ 63፤ በደቡብ ክልል ወልቂጤ 65፤ ሀዋሳ 98 ፤ሆሳእና 89 ፤ዲላ 78፤ አርባምጭ 99፤ ወላይታ ሶዶ 42፤አረካ 53፤ሚዛን 73፤ በቤንሻንጉል ገምዞ አሶሳ 78፤ በአማራ ክልል ባህርዳር 290፣ አንጅባራ114 ፤ እንዲሁም በደሴ ፤ ጎንደር፤ ኮምቦልቻ ፤ ደብረ ማርቆስ እና ፍኖተ ሰላም አብዛኞቹ ቤቶች በክልል የካቢኔ ባለስልጣናት የተያዙ ናቸው፡፡
የግል ቤታቸውን አከራይተው በህዝብ ቤቶች በድሎት በአነሰተኛ ክፍያ በሚኖሩ ባለስልጣናት መንግስት ምንም አይነት እርምጃ አለመውሰዱም ተጠቁሟል።