ሚያዚያ ፰ (ስምንት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በቤንሻንጉል ጉምዝ በህገ ወጥ መንገድ የተፈናቀሉ ኢትዮጵያውያን ወደ ቦታቸው በአስቸኳይ እንዲመለሱና ተገቢው ካሳ እንዲከፈላቸው እንዲደረግ በታዋቂው የአለማቀፍ ህግ ባለሙያ ዶ/ር ያዕቆም ሃይለማርያም አማካኝነት ክስ የመሰረተ ሲሆን፣ ክሱ ሃሙስ ሚያዝያ 9/2006ዓ/ም በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ስምንተኛ ፍትሃ ብሄር ችሎት ላይ መታየት ይጀምራል።
ፓርቲው የቡለን ወረዳ ቀኑን ጠቅሶ ‹‹ስለምትፈናቀሉ ልቀቁ!›› ያለበትን ማስታወቂያና ማስጠንቀቂያዎች በመረጃነት መያዙ ታውቋል።
ሰማያዊ ፓርቲ በአዲስ አበባ ሚያዚያ 19 የተቃውሞ ሰልፍ ለማድረግ እንቅስቃሴ ጀምሯል። ኑ የተነጠቁ መብቶቻችንን እናስመልስ በሚል መሪ ቃል የሚካሄደው ሰልፍ የፖለቲካና የሰብአዊ መብቶች እንዲሁም ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ጥያቄዎች ለመንግስት በድጋሜ የሚቀርቡበት እንደሚሆን ፓርቲው በመግለጫው ጠቅሷል።