ሙሉጌታ ዘውዴ ለሁለተኛ ጊዜ በኖርዌይ የተዘጋጀውን የማራቶን ሩጫ አሸነፈ

ሚያዚያ ፳፪ (ሃያ ሁለት)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በየዓመቱ በሚዘጋጀውን የበርገን ማራቶን ለሁለተኛ ጊዜ ያሸነፈው ሙሉጌታ፣ የኢሳት አርማ ያለበትን ቲሸርት ለብሶ በመሮጥ ለኢሳት ያለውን አድናቆትና ድጋፍ ገልጿል።

ኢትዮጵያዊው አትሌት በኢትዮጵያ በግፍ የታሰሩ የፖለቲካ እስረኞች እንዲፈቱ ፣ ኖረዌይ የህወሃትን መንግስት መርዳቱዋን እንድታቆም ጠይቋል።

ሙሉጌታ ውድድሩን በ 1.09.02. ጨርሷል።

ኢሳት 4ኛ አመቱን በማክበር ላይ ባለበት ወቅት ሙሉጌታ ዘውዴ ያሳየው ድጋፍ የኢሳት ቤተሰቦችንና ደጋፊዎችን አስደስቷል።

አትሌቱ የኢሳትን ቲሸርት ለምን ለመልበስ እንደፈለገ ተጠይቆ ለኢሳት ያለውን ፍቅር ለመግለጽ እንዲሁም በኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን አፈና ለማጋለጥ መሆኑን ተናግሯል።