መንግስት 5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ገዛሁ አለ

የካቲት 16 ቀን 2004 ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመር ራስ ምታት የሆነበት መንግስት፣ ገበያውን ለማረጋጋት 5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ገዝቻለሁ አለ

ከጥር እስከ ሚያዚያ በመላው አገሪቱ የእህል ዋጋ እንደሚቀንስ ቢታወቅም፣ በዘንድሮው አመት ግን ይህ ሲሆን አልታየም። የእህል ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ መጨመሩ ያሰጋው መንግስት ገበያውን ለማረጋጋት 5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ ገዝቶ በማስጋባት ገበያውን ለማረጋጋት እየሞከረ መሆኑን ገልጧል።

ከአንድ ኩንታል ስንዴ እስከ 200 ብር ድጎማ እንደሚያደርግ መንግስት ቢገልጥም አሁንም የአንድ ኩንታል ስንዴ ዋጋ በመንግስት አከፋፋዮች ከ600 ብር በላይ መሸጡ እየተነገረ ነው።

መንግስት በመላ አገሪቱ በቂ የሆነ የእህል አቅርቦት እንዳለ ሲገልጥ ቢቆይም፣ አሁን አሁን ግን የአቅርቦት ማነስ የዋጋ ንረት መንስኤ መሆኑን ለማመን ተገዷል። ግብርናው በ18 በመቶ እንዳደገ እየተነገረ ፣ በሌላ በኩል ደግሞ 5 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ከውጭ እንደተገዛ መነገሩ አብረው የሚሄዱ አይደሉም ሲል ዘጋቢያችን በላከው ዘገባ ላይ አስተያየቱን አስፍሯል።

በርካታ የመንግስት ሰራተኞች የኑሮ ውድነቱን ለመቋቋም ባለመቻላቸው የደሞዝ ጥያቄ በመጠየቅ ላይ እንደሆኑ ይታወቃል።

___________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________________

ESAT is the first independent Ethiopian satellite service tasked to produce accurate and balanced news and information, as well as other entertainment, sports and cultural programming created for and by Ethiopians.

ESAT is committed to the highest standards of broadcast journalism and programming and will strive to provide an outlet of expression to all segments of the diverse Ethiopian community worldwide