ጥቅምት ፳፰ (ሀያ ስምንት) ቀን ፳፻፭ ዓ/ም
ኢሳት ዜና:-በኢጣሊያ ሮም አፍሌ ከተማ ለፋሽስቱ አዶልፍ ግራዚያኒ የተሰራውን መካነ መቃብርና መናፈሻ የተቃወመና እንዲፈርስ የጠየቀ ሰላማዊ ሰልፍ እዚህ ዋሽንግተን ዲሲ ተካሄደ።
ከትላንት በስቲያ በዋሽንግተን ዲሲ በሚገኘው የጣሊያን ኤምባሲ የተደረገው የተቃውሞ ሰልፍ በሶስት ቀን የአውሮፖላን ድብደባና በመርዝ ጋዝ ከሰላሳ ሺህ በላይ ኢትዮጵያን ላስጨፈጨፈው ፋሽስቱ አዶልፍ ግራዚያኒ በታሰቢያ መሰራቱን በጽኑ አውግዞል።
አለም አቀፈ ትብብር ለፍትህ (ገሎባል አሊያንስ ፎር ጀስቲስ) የተሰኘ ድርጅት ባዘጋጀው በዚህ የተቃውሞ ሰልፍ ለጣሊያን ኤምባሲ ደብዳቤ አስገብቶል፤ በፕሮፌሰር ሪቻርድ ፓንግረስት የተላከ መለክትም ተነቦል፡፤ በራሱ በኢጣሊያ መንግስት የጦር ወንጀለኛ ተብሎ 19 አመት ተፈርዶበት ለነበረው አዶልፍ ገራዚያኒ በሮም አቅራቢያ በምትገኝው አፊሊ ከተማ የተሰራው መታሰቢያ በአስቸኮይ እንዲፈርስም ሰልፈኛው ጠይቆል።
የአፊሊ ከተማ ከንቲባ የሆነው ሚስተር ቪሪ ያሰራው ይህን የግራዚያኒ በታሰቢያ በመቃወም ከዋሽንግተን ዲሲ በተጨማሪ በለንደንና በሮምም ተመሳሳይ ተቃውሞ መደረጉን ለማወቅ ተችሎል።