ሃብሊ አዲስ መሪዎችን መረጠ
( ኢሳት ዜና ሃምሌ 2 ቀን 2010 ዓ/ም)የሃረሪ ብሄራዊ ሊግ ሊቀመንበሩ አቶ ሙራድ አብዱልሃዲድ ያጋጠማቸውን ህዝባዊ ተቃውሞ ተከትሎ የድርጅት ሊቀመንበርነት ቦታቸውን ለመልቀቅ መወሰናቸውን ተከትሎ አርብ ሰኔ29 ቀን 2010 ዓም ባደረገው የማእከላዊ ኮሚቴ ስብሰባ አቶ ኦድሪን በድሪን ሊቀመንበር ፣ አቶ ነዲል ማሃዲን ደግሞ ምክትል ሊ/መንበር አድርጎ መርጧል። አዲሱ ሊቀመንበር አቶ ኦድሪን በድሪ ቀጣዩ የክልሉ ፕሬዚዳንት ይሆናሉ ተብሎ ይጠበቃል። አዲሱ ሊ/መንበር ሃረሪ ክልል ውስጥ ኦሮምኛ ተናጋሪ ሃረሪ እንጅ ኦሮሞ የሚባል የለም የሚባል አቋም የሚያራምዱ መሆናቸው በኦሮሞ ማህበረሰብ በኩል ከፍተኛ ተቃውሞ እየገጠማቸው ነው። ወጣቶቹ በበኩላቸው ስር ነቀል እንጅ ጥገናዋዊ ለውጥ አንፈልግም በማለት ተቃውሞአቸውን እየገለጹ ነው። ወጣቶቹ ሊ/መንበሩ የክልሉ ፕሬዚዳንት ሆነው እንዳይመረጡም ግፊት እያደረጉ ነው።