ጥር ፲፬ (አስራ አራት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሶሪያ መንግስት እና የተቃዋሚዎች ተደራዳሪዎች በስዊዘርላንድ የተሰበሰቡ ሲሆን ፣ሁለቱም ተደራዳሪዎች ከማለዳው ሃይለ ቃሎችን ተለዋውጠዋል። የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ሁለቱም ተደራዳሪዎች ወደ ገንቢ ውይይት እንዲመጡ ቢጠይቁም እስካሁን ተስፋ የሚሰጥ ነገር አልተገኘም። አንዱ እና ዋናው አጀንዳ ፕሬዚዳንት በሽር አላሳድ ስልጣን ላይ ስለመቆየታው ሲሆን፣ የአሜሪካው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር ጆን ኬሪ ፕሬዚዳንት ባሽር ስልጣን ላይ የሚቆዩበት ...
Read More »ከሱዳን ጋር የሚደረገው የድንበር ውዝግብ የሞራልና የሶሻል ጥያቄ እንጅ የህግ ድጋፍ የለውም ሲሉ አንድ የኢትዮጵያ መንግስት ከፍተኛ ባለስልጣን ተናገሩ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ባለስልጣኑ ይህን የተናገሩት የመንግስት ከፍተኛ ባለስልጣናትና የደህንነት ሰራተኞች በተገኙበት በተደረገው ግምገማና ውይይት ላይ ነው። በኢትዮጵያ እና በሱዳን መካከል ያለውን ድንበር የማካለል እንቅስቃሴ ከ1965 ዓም ጀምሮ በጊዜው የውጭ ጉዳይ ሚ/ር በነበሩት ዶ/ር ምናሴ ሃይሌና በሱዳኑ አቻቸው ጃፋር ኤሊ ሜሪ መካከል የተጀመረ እና እስካሁኑም የዘለቀ መሆኑን ባለስልጣኑ አውስተዋል። ሱዳኖች “ኢትዮጵያውያን የጉዊን መስመር እየተባለ ...
Read More »በምስራቅ ሃረርጌ ከ59 ሰዎች በላይ መገደላቸውን የኦሮሞ ጥናት ማህበር አስታወቀ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የማህበሩ ፕሬዚዳንት ዶ/ር ኢብራሂም ኢሌሞ ለኢሳት እንደገለጹት ባለፉት ጥቂት ወራት በአንያ፣ ማቶ እና ሙለቄ ቆላማ ወረዳዎች ላይ በፌደራል መንግስቱ እውቅና የተቋቋመውና ስልጠና የሚሰጠው ልዩ ሚሊሺያ እየተባሉ የሚጠሩት ሃይሎች በኦሮሞዎች ላይ በሰነዘሩት ጥቃት 59 ገድለው፣ 42 አቁስለዋል፤ ጉዳት ከደረሰባቸው መካከልም ሴቶችና ህጻናት ይገኙበታል። “በድንበር አካባቢ የሚኖሩ ህዝቦች ሰላም ካገኙ ለተቃዋሚዎች ምቹ ቦታ ...
Read More »አዲሱ የብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሹመት በግል ጋዜጦች ላይ ለሚወሰደው እርምጃ አመላካች ነው ተባለ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የኢትዮጵያ ራዲዮና ቴሌቪዥን ድርጅት ዋና ዳይሬክተር የነበሩት የቀድሞ የህወሃት ታጋይ አቶ ዘርዓይ አስገዶምየኢትዮጵኢያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር በመሆን መሾማቸው መንግስት ከምርጫ 2007 በፊት በፕሬሱ ላይ ለሚወስዳቸው እርምጃዎች ጠንካራ አስፈጻሚ በማስፈለጉ ሊሆን እንደሚችል ኢቲቪን የለቀቁ አንዳንድ ጋዜጠኞች ተናገሩ። የአቶ ዘርዓይ ከቴሌቪዥን ዳይሬክተርነት መነሳት በአቶ በረከት ስምኦን ምትክ የድርጅቱ ቦርድ ሊቀመንበር ሆነው ከወራት ...
Read More »የደቡብ ሱዳን መሪ ተመድን ወቀሱ
ጥር ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በተባበሩት መንግስታት ድርጅት ላይ ወቀሳቸውን የሰነዘሩት ድርጅቱ ራሱን እንደ ሁለተኛ መንግስት በመቁጥር የጦር መሳሪያዎችንና አማጽያንን አስጠልሏል በማለት ነው። ፕ/ር ሳልቫኪር የተመድ ዋና ጸሀፊ አገሪቱን ማስተዳደር የሚፈልጉ ከሆነ በግልጽ ይንገሩን ያሉ ሲሆን፣ ተመድ ወደ አገራቸው ሲገባ ተጓዳኝ መንግስት ሆኖ መግባቱን አላውቅም ነበር ብለዋል። ተመድ በበኩለ በፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር የቀረበውን ...
Read More »የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለአገር ወይስ ለፖለቲካ ስርአቱ ነው የሚል ጥያቄ አነሱ
ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-መንግስት በመረጃዎች አያያዝ ዝርክርክነት ፣ በሳይበር በሚደረጉ ስለላዎች እና ከውስጥ ባሉ የመንግስት አካላት እየሾለኩ በሚወጡ መረጃዎች ህልውናየ አደጋ ላይ ወድቋል በማለት ግመገማ ማድረጉን ተከትሎ “የደህንነት ሰራተኞች ሃላፊነታችን ለማን ነው?” የሚል ጥያቄ ማንሳታቸውን ከደህንነት መስሪያ ቤት ለኢሳት የደረሰው በድምጽ የተደገፈ መረጃ አመለከተ። በስብሰባው ላይ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት እና የመንግስት ሹሞችም ተገኝተው ነበር። ...
Read More »መንግስት የቻይና ኩባንያዎች ላቀረቡት አቤቱታ መልስ ሰጠ
ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ለኢትዮጵያ ከፍተኛ የገንዘብ ብድር የሚሰጡ 2 ባንኮችን ጨምሮ 17 የሚሆኑ የቻይና ኩባንያዎች፣ የመንግስት ባለስልጣናት ስራዎችን ለተወሰኑ የቻይና ኩባንያዎች ብቻ እየሰጡ መሆኑን የሚገልጽ ደብዳቤ ማስገባታቸውን ተከትሎ ፣ የገንዘብ ሚኒስቴር መልስ መስጠቱን ሪፖርተር ዘግቧል። ጋዜጣው እንዳለው መንግስት ቅሬታዎችን ለማስተካከል ቃል ገብቷል። መንግስት የግዢ ስርአት እንደሚዘረጋና የመሰረተ ልማት ተቋማት ኮንትራት እንደ አዲስ እንደሚያዋቅር ገልጿል። ...
Read More »በደቡብ ሱዳን ጦርነቱ ቀጥሏል
ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የውጭ የመገናኛ ብዙሃን እንደዘገቡት በአዲስ አበባ ሁለቱን ተፋላሚ ሃይሎች ለማስማማት ውይይት ቢጀመርም፣ በመሬት ላይ እየተደረገ ያለውን ጦርነት ለማስቆም አልተቻለም። በዩጋንዳ መንግስት የሚደገፈው የመንግስት ጦር ቦር እየተባለ የሚጠራውን ስትራቴጂክ ከተማ ከተቆጣጠረ በሁዋላ በቅርቡ የተነጠቀውን ማላካልን መልሶ ለመያዝ ከፍተኛ ትግል እያደረገ ነው። መንግስት ከተማዋን መልሶ መያዙን ቢያስታውቅም፣ አማጽያኑ ግን ከተማዋ አሁንም በቁጥጥራቸው ስር ...
Read More »በዩክሬን የተነሳው ህዝባዊ ተቃውሞ እንደቀጠለ ነው
ጥር ፱ (አስራ ሁለት) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የፕሬዚዳንት ያንኮቪች መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን በተመለከተ ያወጣው አዲስ ህግ ያስቆጣቸው ዜጎች ወደ አደባባይ በመውጣት ከፖሊሶች ጋር እየተጋጩ ነው። መንግስት የተቃውሞ ሰልፎችን ለመገደብ ያወጣው አዲሱ ህግ በሌሎች የአውሮፓ አገራት ሳይቀር ተወግዟል። ተቃዋሚዎች በፖሊሶች ላይ ድንጋይ ከመወርወራቸውም በተጨማሪ፣ መኪኖችን ሲያቃጥሉ ታይቷል። የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ያንኮቪች ድርጊቱ የዩክሬንን ደህንነት አደጋ ላይ የሚጥል ነው በማለት እርምጃ ...
Read More »የሩዋ ፈለግ ቀበሌ ነዋሪዎች ለሁለተኛ ቀን ከፖሊሶች ጋር ተፋጠዋል
ጥር ፱ (ዘጠኝ) ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በአጽቢ ወንበርታ ወረዳ በሩሃ ቀበሌ ከመስኖ ግድብ ጋር በተያያዘ ሃሙስ እለት የተጀመረው ህዝባዊ ተቃውሞ እስከ አርብ ምሽት የቆየ ሲሆን፣ የወረዳው የአስተዳደር ሰራተኞች እና የደህንነት ሀይሎች አመጹን የቀሰቀሱት እነማን ናቸው አውጡ በማለት ከህዝቡ ጋር እየተወዛገቡ ነው። ህዝቡ በበኩሉ ጥያቄው የህዝብ እንጅ የተወሰኑ ግለሰቦች ባለመሆኑ በግፍ የታሰሩት ሰዎች ይፈቱና ለጥያቄው መንግስት አፋጣኝ ምላሽ ይስጥ ...
Read More »